Sunday, June 16, 2013

በሁሉም የኢህአዴግ የመከላከያ ሰራዊት የጦር ክፍሎች ግምገማ እየተካሄደ መሆኑን ቷውቋል።



በግምገማው እንደ ዋና የመገምገሚያ አጀንዳ ሆነው የቀረቡ ነጥቦች፣-
1-ማንኛውም ወታደር ይሁን ሃላፊ የተሰጠውን ተልእኮ ለመወጣት ያለው የዓላማ ፅናትን በተመለከት
2-ወታደሩ እውቀቱንና ጉልበቱን ሳይቆጥብ ለስርአቱ ህይወቱን ለመስጠት ምን ይህል ዝግጁ ነው?
3-የወታደሩ ዲሲፕሊን ምን ይመስላል?
4-ወታደሩ ልምን  ይከዳል? ፈቃድ ሄዶ ለምን ባለበት ይቀራል?
የሚሉና ሌሎች ነጥቦችን የሚያጠቃልል ሆኖ በተሰብሳቢዎቹ መካከል መተማመን ጥፍቶ እርስ በርሷቸው በጥርጣሬ የሚተያዩበት ሁኔታ መፈጠሩን የደረሰን ዘገባ ያመለክታል።
በተለይም በ 20ኛ ክ/ጦር ግምገማ በተጀመረበት ጊዜ በያንዳንዱ ሰራዊት መካከል አለመተማመንና ጥርጣሬ ተባብሶ ለእረፍት በሚወጡበት ሰዓት በውስጧቸው ስጋት ነግሶ እርስ በራሳቸው የሚፋጠጡበት ሁኔታ ይታያል።
ይህ በእንዲህ እያለ በዓዲ-በራኽና ብላቴ በሚገኙ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ማእከላት ታማኝ የሆኑትን የሰራዊት አባላትን በመመልመል የዳኝነት ስልጠና ወስደው በሰራዊቱ ውስጥ በዳኝነት ተመድበው እዲሰሩ እየተደረገ መሆኑ ለማወቅ ተችሏል።
እንዲህ አይነቱ ስልጠና በአሁኑ ጊዜ ያስፈለገበት ዋና ምክንያት በተለያየ ምክንያት የሰራዊቱ አባላትን እየወነጀሉ ለማሰር ተፈልጎ ሲሆን በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ በሰላም አስከባሪነት ፤ በማእረግ እድገትና ሌሎች ጥቅማጥቅሞች ጋር በተያያዘ የሚነሱ ጥያቄዎችን መልስ ስለማያገኙ በሰራዊቱ የበታችና የበላይ ሽሟሙንቶች መካከል ቅራኔ መፈጠሩን የደረሰን ዘገባ ጨምሮ ያስረዳል።