በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ተቀጥረው የሚሰሩ የመንግስት ሰራተኞች የተሳተፉበት
ሰብሰባ በቅርቡ በአ/አበባ የተካሄደ ሲሆን ፥ በስብሰባው ተሳታፊዎቹ በስርዓቱ ላይ ያላቸውን ቅሬታ ገልጸዋል። የሚከፈለን ደምዎዝ
በቂ ካለመሆኑም በላይ ምክንያቱ በማይታወቅ መዋጮና ከልኩ ያለፈ የመንግስት ግብር ተቆራርጦ በእጃችን የሚደርሰን ጥቂት ገንዘብ ኑራችንን
ለመምራት ተቸግረናል በማለት በአምባገነኑን ስርዓት የሚደርስባቸውን ብዝበዛ መቃወማቸውም ቷውቋል።
ሰራተኛው ለስሙ የምንግስት ሰራተኛ ብንባልም የሚከፈለን የተጣራ ደምዎዝ እዚህ ግባ የሚባል አይደለም ፥በተለይም
በአሁኑ ጊዜ በከተማዋ እየታየ ካለው የኑሮ ውድነት አንጻር ህይወታችንን ማቆየት ፈተና ሆነብናል፣ መንግስት የግለሰቦችን ደምዎዝ
በራሱ ጊዜ ለመቁረጥ ህጉ ባይፈቅድለትም በማን አለብኝነት የሰራተኛውን ደምዎዝ ደርሶ መቁረጡ በሰራተኛው ላይ ዘረፋ እንደፈጸመ ነው
የምንቆጥረው በማለት በስብሰባው ተቋውማቸውን ያሰሙ ሁለት አስተማሪዎች ተሰብሳቢውን አነሳስታችሃል፤ ጸረ-ልማት ናችሁ በሚል ሰበብ
ከስብሰባው ብሁዋላ ከምድብ የስራ ቦታቸው እንዲባረሩ መደረጉን የደረሰን ዘገባ ጨምሮ ያስረዳል።