Sunday, June 16, 2013

በማእከላዊ እዝ የሚገኙ መኮንኖች ከተቃዋሚ ድርጅቶች ጋር ግንኝነት አላችሁ በሚል ሰበብ በስርዓቱ የጸጥታ ሃይሎች እየታፈኑ እንደሚወሰዱ ቷውቋል።


በያዝነው ዓመት ከማንኛውም ጊዜ በላይ የትጥቅ ትግል በማካሄድ ላይ ያሉ የተቃዋሚ ድርጅቶች በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ ገብተዋል የሚል በሰፊው እየተገመገመ ሲሆን ፥ በተለይም በዚሁ ሳምንት ግምገማው ከተራ ወታደሩ አልፎ በመኮኑኑ ላይ ያተኮረ በመሆኑ በሰራዊቱ መካከል ልዩነትና አለመተማመን ተፈጥሯል ፣ ግምገማውን ተከትሎም ታፍነው ወደ አልታወቀ ቦታ የተወሰዱ መኮንኖች መኖራቸውን ለማወቅ ተችሏል።
በዚህ መሰረት ከማ/እዝ ፤ 31ና ክ/ጦር ፤ የ1ኛ ሬጅመንት ስታፍ አባል የነበረ የመቶ አለቃ አዲሱ ሳርሶ የተባለ የብሄረ ኦሮሞ ተወላጅ ከተቃዋሚ ድርጅቶች ጋር ግንኝነት አለህ በሚል ሰበብ በያዝነው ዓመት በተደጋጋሚ ሲገመገም ከቆየ ብሁዋላ በዚሁ ሳምንት ያለ ምንም ማስረጃ ከአ/አበባ በተላኩ የስርዓቱ የጽጥታ ሃይሎች በሌሊት ታፍኖ ወዳልታወቀ ቦታ መወሰዱን የደረሰን ዘገባ ያመለክታል።