Wednesday, June 12, 2013

ከትህዴን ጎን በመሰለፍ አምባገነኑን የኢህአዴግ ስርዓትን በመፋለም ላይ የሚገኙ ታጋይ ቤተሰቦች በጸረ-ህዝቡ ስርዓት በሚደረግባቸው ጫና ከህዝብ እንዲነጠሉ እየተደረገ ነው፣



ኗሪነታቸው በሰሜናዊ ምዕራብ ትግራይ የሆኑ የትህዴን ታጋይ ቤተሰቦች የፈጸሙት ምንም ወንጀል ሳይኖር ልጆቻቸው ከትህዴን ጋር በመሰለፋቸው ብቻ በኢህአዴግ ስርዓት የጸጥታ ሃይሎች መኖሪያ ቤታቸው ቀንም ሆነ ሌሊት ስለሚፈተሽና ቀጣይ ክትትል ስለሚደረግባቸው በቀያቸው በነጻነት መኖር እንዳልቻሉ ከቦታው ከደረሰን ዘገባ ለማወቅ ተችሏል፣
ህዝብን ከማዋከብና ከማሸበር ያለፈ ሌላ ቁምነገር የሌላቸው የስርዓቱ ካድሬዎች በሚጠሩት ማለቅያ የለሽ ስብሰባ ህዝቡን በማስፈራራት እለታዊ ኑረውን እንዳይመራና ተሸማቅቆ እንዲኖር እያደረጉ ነው፣
በተመሳሳይ የኢህአዴግ ስርዓት በፈጠረው የፍጆታ እቃዎች ዋጋ በከፍተኛ ደረጃ መጨመር የራማ ከተማ ኗሪዎች ችግር ላይ መውደቃቸውን ከቦታው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል፣