የያለምብርሃን ሆስፒታል የልኡካን ቡድን አባላት ግድቡ እየተገነባበት ባለው ቦታ በደረሱብት ጊዜ በቦታው
በሚገኙ ጉዳዩ የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት የስራውን ሂደት የተመለከተ አጭር ገለጻ ተደርጎላቸዋል ፣የልኡካን ቡዱኑ አባላት
ከተሰጣቸው ገለጻ በመነሳት ካቀረቡት በርካታ ጥያቄዎች መካከል የኢትዮጵያ ህዝብ ባጠቃላይ ለዚሁ ግድብ ማሰሪያ የሚሆን ገንዘብ እያዋጣ
መሆኑን ይታወቃል ፥ ነገር ግን ከተዋጣው ገንዘብ ጋር የሚመጣጠን ስራ እየተሰራ አይደለም ፣ በህዝቡ እየተዋጣ ያለው ገንዘብ ለምን
ስራ እየዋል ነው? የሚል ይገኝበታል።
በተለይም መንግስትን በመወከል ፕሮጀችቱን በመምራት ላይ ያሉት ኢንጂነር ስመኘው በቀለ “እኛ መንግስት በመደበልን
በጀት መሰረት የአቅማችንን እየሰራን ነው፣ ከተመደበልን በጀት የባከነ ነገር የለም ፣በመሰረቱ ፋሽኑ ያለፈበትን ጥያቄ ነው እያቀረባችሁት
ያለ ፣ እናንተ ለጉብኝት ሳይሆን ለሌላ ተልእኮ ነው የመጣችሁት ” በማለት ቁጣ የተቀላቀለበት ምላሽ በመስጠታቸው የልኡካን ቡዱኑ
አባላት በሁኔታው ተደናግጠው ወደ ቦታቸው ለመመለስ መገደዳቸውን ከቦታው የደረሰን ዘገባ ጨምሮ ያስረዳል።