Sunday, February 23, 2014

በፍኖተ ሰላምና ኮሶበር ከተማ ውስጥ ከየካቲት 4/ 2006 ዓ/ም ጀምሮ እየተካሄደ ያለው ስብሰባ 2007 ዓ/ም ለሚደረገው ምርጫ ማእከል ያደረገደ ቢሆንም አብዛኛዎቹ በስብሰባው የተሳተፉት ወገኖች ግን በአጀንዳው ደስተኞች እንዳልሆኑ ምንጮቻች ከቦታው አስታወቁ።



በአማራ ክልል ምእራብ ጎጃም ዞን ፍኖተ ሰላም ከተማ  በሚገኘው ቤዛን ዳሞት ሆቴልና፤ በአዊ ዞን ኮሶበር ከተማ በሚገኘው አዳራሾች ውስጥ እየተካሄደ ያለው ስብሰባ የስርአቱ አመራር አካሎች የስብሰባው አጀንዳ በመጪው ዓመት በሚካሄደው አገራዊና ክልላዊ ምርጫ ላይ ተቃዋሚ ድርጅቶች እንዲዳከሙና ኢህአዴግ ሙሉ በሙሉ እንዲያሸንፍ ለማድረግ እያንዳዱ አመራር የበኩሉን ሚና መጫወት አለበት የሚል መልእክት ቢኖረውም እየተካሄደ ባለው ስብሰባ ግን ቁጥራቸው ጥቂት የማይባሉ ተሳታፊዎች አጀንዳውን ስላልተቀበሉት ደስተኞች እንዳልሆኑ ለማወቅ ተችለዋል።
     ይህ በበላይ አመራሮችና ካድሬዎች በኩል በሁሉም ዞኖችና ወረዳዋች እየተካሄዱ ያሉ ስብሰባዎች ጭንቀት የወለደውና መጪው 2007 ዓ/ም በወያኔ ኢህአዴግ ሊካሄድ በታሰበው አስመሳይ ምርጫ ላይ በምን መንገድ ለተቃዋሚ ድርጅቶች ማዳከም እንደሚቻልና ለስርአቱ አባላት ገንዘብና ሌሎች ጥቅማ ጥቅም ሰጥተህ ወደ እጅህ ታስገባዋለህ የሚል መልእክት ያለው እንጂ የሃገርና የህዝብ ጉዳይ የሚመለከት  እንዳልነበረ አንዳንድ በስብሰባው ውስጥ የተሳተፉ ወገኖች ለምጮቻችን በሰጡት መረጃ ለማወቅ ተችለዋል።