እነዚህ ከተወሰኑ ቤተሰቦች ውስጥ መጥተው ሃላፊነቱን የተቆናጠጡት ግለሰቦች፣-
ወ/ሮ አለሚቱ አለነ የኮምኒከሽን ሃላፊ፤ አቶ መላኩ አለነ የወረዳዋ አስተዳዳሪ፤ አቶ ገበዮህ የፖለቲካ ክፍል ሃላፊ፤ አቶ አዲስ
ብርሃኑ የማህበራት ሃላፊ፤ አቶ ሰሎሞን ደሴ የሲቪል ሰርቪስ ምክትል ሃላፊ፤ አቶ እሱባለው ይሁን የእርሻ ልማት ፅ/ቤት ሃላፊና
አቶ ባይሞት መኩርያ የእርሻ ልማት ፅ/ቤት ምክትል ሃላፊ ናቸው።
በዚገም ወረዳ የሚገኙ በዘመድ አዝማድ የተሳሰሩ ሃላፊዎች። በወረዳው
የአቅም ግንባታ ጽ/ቤት ለማሰራት በሚል ምክንያት 1.2 ሚልዮን ብር ከኢኮኖሚያዊ ልማትና ፋይናንስ ክፍል ሃላፊ አቶ ስመላለም ምህረቱ
ጋር ሆነው በኮሚቴ ወስነው ወጪ በማድረግ ይገነባል የተባለው ፅ/ቤት መሰረቱ እንኳን ሳይጀመር ተጨርሰዋል በማለት ገንዘቡን ለግል
ጥቅማቸው እንዳዋሉትና። በዚሁ የተበላሸና ቤተሰባዊ የሆነ የወረዳዋ ሃላፊዎች አሰራር። አብዛኛው የአካባቢው ህዝብ ተቃውሞውን በመግለፅ
ላይ እንደሆነ ታውቀዋል።
ይህ በእንዲህ
እንዳለ በዞኑ ፅ/ቤት ውስጥ የሚገኙ ሃላፊዎች ከሦስት ቤተሰቦች የተውጣጡ ሲሆን። እነሱም አቶ ባዘዘው ጫኔ የዞኑ ዋና ኣስተዳዳሪ፤
ኣቶ የኔ ንጉስ የውሃ ልማት ፅ/ቤት ሃላፊ፤ አቶ ግርማ ታፈረ የእርሻ ልማት ሃላፊ፤ አቶ ወንድም የማህበራት ፅ/ቤት ሃላፊና አቶ
ሚናስ የፀጥታ ክፍል ሃላፊ ሲሆኑ በአጠቃላይ የሚያስተላልፉት ውሳኔም ቅንነት የሌለው፤ በዘመድ አዝማድና በእከክልኝ ልከክልህ የተመሰረተ
አሰራር እንደሚከተሉ መረጃው አስታውቀዋል።
ከኣዊ ዞን
ሳንወጣ አቶ መዝገቡ አለበል የተባሉ ቀደም ሲል የዚገም ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ የነበሩ ግለ ሰብ የአካባቢው ህዝብ ባደረገው ግምገማ
ከአልፋ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ የሃሰት ድግሪ በመያዝ ወደ ስራ እንደገቡና በዚህም ምክንያት መምራት አይችልም ተብሎ ቢገመገምም በአዊ
ዞን የብአዴን ድርጅት ፅ/ቤት ሃላፊ የሆነው አቶ አየን ብርሃነ የተባለው የስርአቱ ካድሬ ግን ለዚሁ ግለሰብ ታታሪና ቀና ሰው ነው
በሚል ሽፋን። ከቦታው ቀይሮ በጓንጓ ወረዳ የገጠር መንገድ ፅ/ቤት ሃላፊ ሆኖ እንዲሰራ በመሾሙ ምክንያት ይበልጥ የህዝቡንና የሃገሪቱን
ሃብት እየመዘበረ መሆኑን መረጃው አክሎ አስረድተዋል።
ባሁኑ ወቅት ኣቶ መዝገቡ ኣለበል ከደብረ-ማርቆስ ወደ ሱዳን እየተሰራ
ባለው ኣዲስ መንገድ ከቁጭ አየሁ እስከ ዚገም የሚደርሰው ጃሞራ መንገድ ወደሚባለው ቀበሌ መንገድ ይሰራል በሚል ምክንያት ‘‘ ከኣዊ
ማህበር ፍቅር ኢንቨስተሮች ’’ 60 ሺ ብር፤ ከኣካባቢው ነዋሪ ህዝብ ከ 45 ሺ ብር በላይ ገንዘብ ተቀብሎ ሲያበቃ የተባለው መንገድ
ሳይሰራ ቀርቶ ገንዘቡን ለግለ ጥቅሙ ኣውሎታል የሚል ትልቅ የህዝብ ስሜት አስነስቶ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችለዋል።