Friday, February 21, 2014

በትግራይ ምዕራባዊ ዞን ማይካድራ ከተማ የሚገኙ ወጣቶች በስርዓቱ የፖሊስ አባላት በደል እየተፈፀመባቸው እንደሚገኙ ምንጮቻችን ገለፁ።



በመረጃው መሰረት በማይካድራ ከተማ የሚገኙ የፖሊስ አባላት ለወጣቶቹ ከመኖርያ ቤታቸው አስገድደው በመውሰድ ዳብዛቸውን እያጠፍዋቸው እንደሚገኙ በመግለፅ ከነዚህም ውስጥ አንዱ ወጣት የማነ ጵጥሮስ እንደሆነ ተገልፅዋል።
ወጣት የማነ የትህዴን ታጋዮች ወደ ከተማዋ ገብተዋል የሚል ወሬ በሰማበት ግዜ። በመዝናኛ ክበቡ ውስጥ ለነበሩ ሰዎች  ደስታውን ለመግለጽ ቢራ ከጋበዛቸው  በኃላ የፖሊስ ኣባልት የካቲት 2/2006 ዓ.ም ወደ መኖርያ ቤቱ በመሄድ አፍነው ወደ በረሃ በመውሰድ በዱላ ደብድበው በኪሱ የነበረውን 1000 ብር አውጥተው እንደውሰዱት መረጃው አስትውቁዋል።
ቤተሰቦቹ ወደ ህክማና ለመውሰድ እንዲፈቀድላቸው ለፖሊስ አባላት ላቀረቡት ጥያቄ ሰሚ አካል እንዳላገኙ የገለፀው መረጃው። ለዚህ ሃላፈነት የሌለውና ጭካኔ የተሞላው አካሄድ የታዘቡ የከተማዋ ነዋሪዎች። ይህ ስርዓት ከደርግ የባሰ ነው በማለት ምሬታቸውን በመግለፅ ላይ እንደሚገኙ ለማውቅ ተችልዋል።