Monday, April 7, 2014

ገብረሂወት መርዙ በመባል የሚታወቀው የትግራይ ሰሜናዊ ምእራብ ዞን አስተዳዳሪ ስብሰባ በመምራት ላይ እንዳለ መርዝ የገባበት ውሃ ጠጥቶ እንደሞተ ምንጮች ከሽሬ እንዳስላሴ ከተማ ገለፁ።



በህወሓት የበላይ አስተዳዳሪዎች ላይ የተከሰተው ግላዊ ጥቅም መነሻ ያደረገና ረጅም ግዜ ያስቆጠረው እንካስላንትያ ለመፍታት ተብሎ በቅርብ ግዜ የዞኑ አስተዳዳሪ ሆኖ በስርአቱ ሹመት የተሰጠው የህወሃት ታጋይ የነበረው ገብረሂወት መርዙ ባለፉት ቀናት ስብሰባ እየመራ በነበረበት ሰአት የስራ ባለደርቦቹ መርዝ የገባበት ውሃ አስጠጥተው እንደገደሉት የደረሰን መረጃ አስታውቀዋል።
    ይህ በሰሜናዊ ምእራብ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ገብረሂወት መርዙ የተወሰደው የግድያ እርምጃ በድርጅቱ የበላይ ባለስልጣኖች ውስጥ የነበረው ግላዊ ጥቅም መነሻ ያደረገ ጥላቻ ከፍተኛ ደረጃ የደረሰ መሆኑን የገለፀው መረጃው የህወሃት ባለስልጣኖች ህዝቡን ለማታለል አስበው ራሳቸውን ለፈፀሙት የግድያ ሂደት ምንም እንደማያውቁ በማስመሰል አስከሬኑ መቀሌ በሚገኘው አይደር ሪፈራል ሆስፒታል ወስደው እንዲመረመር ማድረጋቸው ተገለፀ።
    በገብረሂወት መርዙ የቀብር ስነ ስረት ላይ ፀረ ህዝብና የትግራይ ክልል ርእሰ መስተዳደር አባይ ወልዱ በተገኘበት መጋቢት 2006 ዓ/ም እሁድ ቀን እንዳስላሴ አቡነ አረጋዊ ቤተክርስትያን እንደተፈፀመ መረጃው አክሎ አስረድተዋል።
    ባለፈው የዜና እወጃችን በህወሃት ባለስልጣኖች መሃል ግለኝነት አስተሳሰብ የተጠናወተው ያለመስማማት በከፍተኛ ደረጃ እየታየ መሆኑንና በዚህም ምክንያት ትልቅ ውጥረት ላይ እንደሚገኙ መግለፃችን ይታወቃል።