Friday, April 11, 2014

የወያኔ ስርአት ዋነኛ ተግባር ቅጥፈትና ክህደት ነው!



የዜጎቹን ጥቅም ከማስቀደም ይልቅ የራሱና የግብረአበሮቹን ፍላጎት ለሟሟላት የሚንቀሳቀስ ህዝባዊ ድጋፍና መሰረት የሌለው ስርአት የስልጣኑን እድሜ እስከሚያበቃ ድረስ ማደናገር ማእከል ያደረገ ፀረ ህዝብ ድርጊት በመፈፀም ተግባር ላይ ግዜውን ያሳልፈዋል።
    በአንዳንድ አገሮች እንደምናየውና እንደምንታዘበው መሪዎች በህዝብ ተመርጠው ይሁን አመፅን ተጠቅመው ወደ መንበረ ስልጣን ሊወጡ በሚቀራረቡበት ግዜ አገሪቱና ህብረተሰቡን ለመጥቀም ሲሉ መስዋእትነት እንደሚከፍሉና ዲሞክራሲያዊ ስርአት ለማስፈንና የተቀላጠፈ እድገት ለማረጋገጥ ብለው ቃል በመግባት ወደ ስልጣን እንደሚወጡ ይታወቃል።
    ለመግብያ እንዲሆነን ይህን ካልን ዘንዳ አጠቃላይ የወያኔ ኢህአዴግ ስርአት ከላይ ለመጥቀስ እንደተሞከረው ለማያያዝ ያህል አንዳድ ቁምነገሮች እናስቀምጥ፣ ስርአቱ ከመጀመርያው የትግል ወቅት ጀምሮ የደርግ ስርአት እስኪደመሰስ ድረስ ሲያራምደው የነበረ የማደናገር ሂደትና በታጋዮቹና በህብረተሰቡ ላይ ሲያስተጋባቸው የነበረው አስመሳይ የተስፋ ቃላቶች ተዘርዝረው የሚያልቁ አይደሉም።
    ትግላችን ለፍትህና ለዴሞክራሲ ነው ከሚለው ቀለል ያለ አባባል ጀምሮ  ህብረተሱቡ እንደ ህዝብ ይሁን እንደ ግለ ሰብ ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቱ እንዲከበርለት በተለይ በትግሉ ወቅት አስፈላጊውን ድርሻ ላበረከተ የህዝቡ ወገን የሆነው ጀግናው ሃርበኛ በተገኘው የድል ውጤት ተጠቃሚ እንደሚሆንና በሰራው ገድል ክብርና ሞገስ እንደሚገባው ከመጠን በላይ ተነግሮለታል።
    ቢሆንም ግን መድረኩ ሙሉ በሙሉ ተቀይሮ እነዛ በትግሉ ግዜ ለህብረተሰቡ ጥቅም ብለው እንደታገሉ የሚናገሩ በዚያኛው ወቅት የትግሉ መሪዎች ባሁን ግዜ ያገር ባለስልጣናት ሆኖው ያሉ ከሃድያን ድሮም ቢሆን ለማስመስል እንጂ ለህዝቡ ጥቅም ብለው እንዳልታገሉ በተግባራቸው አስመሰኩረውታል።
    የወያኔ ስርአት መሪዎች ስልጣናቸው በጭቁኑ የታጋዩ ደምና መስዋእትነት ያገኙት መሆናቸው እያወቁ በአጠቃላይ ለሁሉም ህብረተሰብ በተለይ ደግሞ ከጎናቸው ሳይለዩ ቀና አስተሳሰብ ይዘው ሲታገሉ አካላቸው ለተጎዱ ጀግኖች በላያቸው ላይ ግልፅ የሆነ ክህደት እንደፈፀሙ በተለያዩ መድረኮች ተገልፀዋል።
ባለፈው ሳምንት በወያኔ ስርአት ከፍተኛ በደል ደርሶባቸው ወደ ዳንሻ እንዲሄዱ የተደረጉ  ከፍተኛ መኮንኖች የሚገኙባቸው በርከት ያሉ የቀድሞ የህወሓት ታጋዮች ስልጣን ላይ እንዲወጣ ያደረግነው መንግስት ሸፍጠኛና ከሃዲ ነው በማለት በአካባቢያቸው በተደረገው ስብሰባ ላይ ሃሳባቸው ገልፀዋል።
     እነዚህ ከሰራዊት ተሰናብተው ወደ ዳንሻ እየሄዱ በነበሩበት ወቅት ማህበራውና ኤኮኖሚያዊ ፍላጎታቸው አስመልክቶ በመንግስት እንደሚሟላላቸው ቃል የተገባላቸው ቢሆንም ተግባር ላይ ግን ለእርሻ ከሚሆን መሬት በስተቀር አንዳችም እገዛ እንዳልተደረገላቸው በመግለፅ የህወሃት መንግስት የተናገረው ቃል የማያከብርና ከሃዲ ስርአት እንደሆነ በስብሰባው ውስጥ ሃሳባቸውን በግልፅ አንፀባርቀዋል።
     ለህዝብና ለሃገር ነፃ ለማውጣት ብለው ባለፈው የትግል ወቅት ሂወታቸው መስዋእት ያደረጉና በኋላም በወያኔ አመራሮች ቀጥታዊ ትእዛዝ ወደ ዳንሻ ከተጓዙ ጀግኖች ውስጥ ኮለኔል ደመቀና ሻለቃ አሸብር የተባሉ የቀድሞ የህወሃት ታጋዮች በህወሃት መንግስት እምነት የጣለና ውሃን ቅቤ ያወጣል ብሎ የናጠ አንድ ነው በማለት ህዝቡን በተሰበሰበበት ቦታ በገለፁበት ግዜ በወቅቱ የነበረው ተሳታፊ ለሰጡት አስተያየት ሰምቶ ከጎናቸው እንዳለ ለማሳየት ድጋፉ በጭብጨባ ገልፆላቸዋል።
    የወያኔ ስርአት የሚፈልገውን ነገር እስኪያገኝ ድረስ። የህዝቡን ወገን እንደሆነ፤ ለህዝብና ለአገር ጥቅም ብሎ የማይከፍለው ዋጋ እንደሌለና ለማስመሰል ብሎ የማደናገሪያ ስልቱ የሚጠቀም መሆኑ ቢታወቅም አሁንም እንዳለፈው እንደ እስስት እየተቀያየረ ሁሌ እንደሚጠቀምበት ህዝቡን የማደናገር ብልሃቱ ለማስቀጠል የአባይ ግድብ የመጪውዋ ኢትዮጵያ የእድገት መሰረት እንደሆነ አስመስሎ ከጭቁኖች እጅ በቢልዮን የሚቆጠር ሃብት እየነጠቀ ለግንባታው እየተሯሯጠ ይገኛል።
    ለአባይ ግድብ ግንባታ የሚቃወም ኢትዮጵያዊ ባይኖርም የወያኔ ስርአት እንደሚለውና ግድቡ ለአገራችን የእድገት ጎዳና በር ከፋች እንደሆነ አድርጎ እንደሚገልፀው ሳይሆን አባይ ቢገደብ  የመጨረሻው ፍሬ ተቋዳሽ ህዝቡ ሳይሆን። የሹማምንተኞቹ ኪስ ማደለብያ እንደሚሆን ቅንጣት ያህል የሚያጠራጥር ነገር የለውም። ምክንያቱም! የወያኔ ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ስርአት ዋነኛ ተግባር ቅጥፈትና ክህደት ስለሆነ።