Wednesday, April 9, 2014

የኢ.ህ.አ.ደ.ግ ከፍተኛ የሰራዊት መኮንኖች በሰራዊቱ ያላቸው አመኔታ ከግዜ ወደ ግዜ እያሽቆለቆለ በመሄዱ ምክንያት ለስራ ተብሎ የተሰጣቸውን የጦር መሳሪያ በመሸጥ ላይ እንዳሉ ተገለፀ።



ከነዚህ መሳሪያ በመሸጥ ላይ የተሰማሩ መኮንኖች የ22ኛ ክፍለ ጦር አባሎች ውስጥ ሻምበል ዮውሃንስ አማረና የመቶ አለቃ ብርሃኑ መገርሳ የተባሉትና ሌሎች እንደሆኑ የገለጸው መረጃው እነሱ ከመሳሪያ ግምጃቤት አውጥተው በታርጋ ቁጥር 6508 የመከላከያ ተሽከርካሪ  7ሺ ጥይትና 15 ክላሽ ጭነው እየተጓዙ ደባርቅ ከተባለው ከተማ ሲደርሱ እንደተያዙ የመጣልን መረጃ አመለከተ።
መረጃው አክሎ ሊሸጡት የጫኑትን መሳርያ እንዳይነቃባቸው በሬሳ ሳጥን ኣሽገው ሊያሳልፉት ሲሞክሩ ደባርቅ ከተማ ሲደርሱ ከግብረ አበራቸው አቶ ኣብርሃ በርሀ ለሚባለው የዓዲ ዳዕሮ ተወላጅ ከሸጡለት በኃላ በተደረገው ክትትል ሻጮችና ገዥዎች ሊያዙ መቻላቸውን ለማወቅ ተችለዋል።