Wednesday, July 30, 2014

በኦሮሚያ ክልል ናዝሬት ከተማ የኦህዴድ ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ አባል ያልሆኑ ነጋዴዎች ዋጋ ጨመራችሁ በሚል ሰበብ ድርጅታቸው እየተዘጋ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፣፣



በናዝሬት ከተማ ምግብ ቤቶችን ከፍተው ቤተሰቦቻቸውን ሲያስተዳድሩ የቆዩ ከ28 በላይ የኦህዴድ አባላት ያልሆኑ ዜጎች አባል ባለመሆናቸው ብቻ የገበያ ዋጋ ጨምራችኋል በሚል ሰበብ በገዥው ፓርቲ ድርጅታቸው የታሸገ መሆኑን ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመለከተ፣፣
    በተመሳስይ መንገድ በአማራ ክልል ፍኖተ ሰላም ከተማ ከ20 በላይ የሚሆኑ ነጋዴዎች ከተቃዋሚ ድርጅቶች ጋር እየተገናኛችሁ የገበያ ዋጋ እንዲጨምር ታደርጋላችሁ በሚል ከብአዴን ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ባለ-ስላጣናት ማስጠንቀቂያ የደረሳቸው መሆናቸውን ከስፍራው ምንጮቻችን አስረድተዋል፣፣
    የገበያ ዋጋ እየጨመራችሁ ነው በሚል ስም በንፁሃን ወገኖች ላይ እየተወሰደ ያለው የንግድ ድርጅታቸውን የመዝጋት ተግባር በመላው ሃገሪቱ ሊካሄድ እየታሰበው ላለው የ2007ዓ/ም ምርጫ ህዝቡን በማስፈራራትና በገንዘብ ሃይል በማባበል ከጎኑ እንዲሰለፍ ለማድረግ መሆኑን አንዳንድ ምሁራን እየገለጹ እንደሚገኙ ከመርጃው ለማወቅ ተችሏል፣፣