Wednesday, July 30, 2014

በታሕታይ አድያቦ ወረዳ ልዩ ስሙ ዓዲ ቦኹራይ በተባለ ቦታ ሲሰለጥኑ የቆዩ የማዕከላዊ እዝ ሰልጣኝ መኮነኖች የተመደበላቸው በጀት በሃላፊዎቻቸው እንደተበላ ምንጮቻችን አስረዱ፣፣



ከማዕከላይ እዝ ሾልኮ የደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተው በታሕታይ አድያቦ ወረዳ ልዩ ቦታ ዓዲ ቦኽራይ በተባለ ቦታ ሲሰለጥኑ የቆዩ ማዕረጋቸው ከሻምበል በላይ የሆኑ የማዕከላይ እዝ መኮነኖች ለነሱ መሰልጠኛ ተብሎ የተመደበ ከ600 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ኮለኔል ከበደ ፍቃዱ የተባለ የማዕከላይ እዝ ማሰልጠኛ ሓላፊ ለግል ጥቅሙ እንዳዋለው ታወቀ፣፣
    መረጃው ጨምሮ እንዳስረዳው ለነዚህ ሰልጣኝ መኮነኖች ሓምሌ 10/2006/ዓ.ም ሜጀር ጀኔራል የውሃንስ ወልደገርግስ ሰብስቦ ባካሄደላቸው ግምገማ ላይ የተመደበልን በጀት ተጠፋፍቷል ብለው በተናገሩበት ሰዓት ሜጀር ጀኔራል የውሃንስ ወልደገርግስ በበኩሉ እኛ ለማሰልጠኛ የሚሆን በቂ በጀት በጅተናል ስለዚህ ይህንን ገንዘብ ያጠፋው አካል ይጠየቅበት እንጂ እኔ በበኩሌ የማደርገው ነገር የለኝም የሚል አሳፋሪ መልስ ለሰልጣኞች በሰጠበት ሰዓት በርከት ያሉ ስልጣኝ መኮነኖች በከባድ ስሜት ውስጥ ገብተው እንደሚገኙ ያገኘነው መረጃ አክሎ አስረድቷል፣፣