Wednesday, July 30, 2014

በሽሬ ከተማ ለሚኖሩ የአረና ድርጅት አባላት በህወሃት ኢህአዴግ ካድሬዎች በቤታቸው በር ላይ የማስፈራርያ ወረቄት እየተለጠፈባቸው መሆኑን ተገለፀ፣፣



    የአረና ትግራይ ድርጅት አመራሮችና አባላት በስርአቱ ካድሬዎች ተይዘው እየታሰሩ፤ እየተደበደቡና እየተገደሉ መሆናቸውን የገለፀው መረጃው ነዋሪነቱ በሽሬ እንዳስላሴ ከተማ የሆነው አቶ አያሌው በየነ ለተባለው የአረና ድርጅት አባል ያንተ እድልም ልክ እንደ ጓደኞችህ ይሆናል በማለት የስርአቱ ካድሬዎች ሓምሌ 12/2006ዓ/ም በመኖርያው ቤቱ በር ላይ በሌሊት የማስፈራርያ ወረቀት ለጥፎውበት ያገኘነው መረጃ አስታወቀ፣፣
   ቀደም ሲል አቶ አያሌው በከተማው ተከራይቶ እየኖረ ቢቆይም ገብረመድህን የተባለው የፖሊስ ሃላፊ ኢንስፔክተር ለአከራዮቹ ከቤታቹህ አስወጡት እያለ እያስፈራራቸው መቆየቱና ለተባዳዩም ቢሆን ከቦታው እንዲወጣ የማስፈራርያ ወረቄት ከእንስፔክተሩ  ይደርሰው እንደነበር ምንጮች ከቦታው አስረድተዋል፣፣
    በመጨረሻ መረጃው እንዳስታወቀው አቶ አያሌው በቤቱ በር ላይ የማስፈራርያ ወረቄት ተለጥፎ በማየቱ ምክንያት በከባድ ስጋት ላይ ወድቆ መቆየቱና ባሁን ግዜም የት እንደገባና ሁኔታውን በተመለከተ በምን ደረጃ ላይ እንዳለ እንደማይታወቅ መረጃው እክሎ አስረድተዋል፣፣