Friday, October 31, 2014

በአማራ ክልል አብደራፍዕ ከተማ የሚገኙ ፖሊሶች ወጣቶችን ጠለፍው ወደ በረሃ በመውሰድ እየገደሉአቸው እንዳሉ ከአካባቢው ያገኘነው መረጃ አመለከተ፣




በምንጮቻችን መረጃ መሰረት በአብደራፊ ከተማ በበላይ ሃላፊዎች ትዕዛዝ ግደሏቸው ለተባሉ ንፁሃን ዚጎቻችን ምሸት ወደ በረሃ በመወሰድ መግደላቸውን  የገለፀው መረጃው። በዚህ መሰረትም ሓጎስ እንባየ ለተባለ ወጣት ጥቅምት 11 /2007 ዓ.ም እንደገደሉትና። ህዝብ እንዳይነቃባቸውም ሰሊጥ ሲሰርቅ ተገኝቶ ነው የተገደለው እንዲባል በሟቹ እጅ ሰሊጥ በማስቀመጥ በተከመረ ሰሊጥ እንደደበቁት ለማወቅ ትችሏል፣
   መረጃው በመጨረሻ።- ለወጣት ሓጎስ እንባየ የገደለ አሻግሬ የተባለ የፖሊስ አባል እንደሆነ የገለፀው መረጃው። ይህ በኢህአዴግ ፖሊሶች እየተፈፀመ ያለው ንፁሃን ዜጎችን የመግደል እኩይ ተግባርም። በአብደራፍዕ ከተማ ብቻ ሳይሆን በሁሉም የሃገራችን አካባቢዎች እየተፈፀመ ያለ አረመኔያዊ ተግባር እንደሆነና በህዝቦች መካከልም መነጋገርያ አጀንዳ ሆኖ እንደሚገኝ ምንጮቻችን አክለው አስታወቀዋል፣