በትግራይ ክልል ማእከላዊ ዞን፤ አህፈሮም ወረዳ ከሚገኙት አዳጊ ከተማወች
አንዷ የሆነችው የድብድቦ ከተማ ነዋሪዎችዋ በመብራት ሃይል እጥረት ከተቸገሩ ረጅም ቀን ቢያስቆጥሩም፤ ነዋሪዎች ያጋጠማቸውን ችግር
እንዲፈታላቸው በማለት በተደጋጋሚ ጥያቄ የሚያቀርቡ ቢሆኑም ስልጣን ላይ ያለው ስርአት ግን ችግሩን ለመፍታት ትኩረት ባለማድረጉ፤
ህዝቡ እለታዊ ንሮውን ለሟሟላት ሲል የአምስት ሰአት መንገድ በእግሩ እየተጓዘ የእህል ወፍጮ እንዲጠቀም መገደዱን የተገኘው መረጃ
አስታውቋል።
በተመሳሳይ የስኳር አቅርቦት ባለመኖሩ ለአንድ ኪሎ ስኳር እስከ 80 ብር በሚደርስ
እየተሸጠ መቆዮቱንና፤ የስርአቱ ካድሬዎች ግን ምርጫው እየተቃረበ ባለበት በአሁኑ ጊዜ ከየት እንዳመጡት የማይታወቀው ስኳር ለአንድ
ኪሎ በ16 ብር ሂሳብ እያከፋፈሉ ያከፋፈሉ መሆናቸውና፤ ይህንን የተንኮል አሰራር የታዘበው ህዝብም ባጭር ጊዜ ውስጥ ይህን ያህል
ዋጋ መቀነሱ ምን የተሰራ አዲስ ነገር አለ በማለት፤ ድርጊቱ ምርጫን ታሳቢ በማድረግ የተደረገ መላ ነው። ምርጫው ካለፈ በኃላም
አይደገምም በማለት በግልፅ እየተነጋገረቡት መሆኑን የደረሰን መረጃ አክሎ አስረድቷል።