Friday, March 13, 2015

በጎንደር ከተማ የሚገኙ የኢህአዴግ ስርዓት ወታደሮችና ፖሊሶች እራስ በራሳቸው እየተገዳደሉ እንደሚገኙ ምንጮቻችን ከጎንደር ከተማ አስታወቁ።



    በምንጮቻችን መረጃ መሰረት በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ከተማ የሚገኙ የኢህአዴግ ስርዓት የፖሊስ አባላትና ወታደሮች በተለያዩ ወቅቶች አድማዎችን እያስነሱ እርስ በራሳቸው በመገዳደል ላይ እንደሚገኙና በተመሳሳይ አሁንም የካቲት 8/2007 ዓ/ም በጎንደር ከተማ ተስፋይ ግርማይ የተባለ የ24 ክፍለ ጦር ኦፕሬተር  ወርቁ አራጋው የተባለውንም ፖሊስ በሽጉጥ ገድሎት እንደጠፋ ለማወቅ ተችሏል።
    መረጃው አክሎ የኢህአዴግ የፖሊስ አባላትና ወታደሮች  በስርዓቱ ላይ ያላቸው እምነት እያሽቆለቀለ በመሄድ ላይ በመሆኑ  ምክንያት የተረጋጋ ህይወት ስለሌላቸው እርስ በራስቸውና አመራሮቻቸውን በመግደል ላይ እንደሚገኙና በተለያዩ መጠጥ ቤቶች በመግባትም ሲቪል ህብረተሰብ በመግደል ስራ ላይ ተሰማርተው እንደሚገኙ የደረሰን መረጃ አክሎ አስታውቋል።