Thursday, March 5, 2015

በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን ልዩ ስሙ አብርሃ-ጂራ በተባለው ቦታ የሚገኙ የትግራይ ተወላጅ የሆኑ መምህራንና ተማሪዎች ከነበሩበት ትምህርት ቤት እንደተባራሩ ምንጮቻችን ከስፍራው አመለከቱ።



  ምንጮቻችን ከስፍራው እንደገለፁት በአማራ ክልል ስሜን ጎንደር ዞን ልዩ ስሙ አብራ-ጂራ በተባለው ስፍራ የሚገኙ የትግራይ ተወላጅ መምህራንና ተማሪዎች ወገኖቻችን ቀደም ሲል በሁለቱ ክልሎች መካከል ተፈጥሮ የነበረውን ግርግር ተከትሎ መምህራንና ተማሪዎች የካቲት 9 ቀን 2007 ዓ/ም በብአዴን ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ካድሬዎች እየተያዙ ከሚያስተምሩበትና ከሚማሩበት ትምህርት ቤት እንደተባረሩ አስረድተዋል።
   የችግሩ ሰለባ የሆኑ ዜጎቻችን ይህንን ሃላፊነት የጎደለው የትምህርት ማደናቀፍ አስፀያፊ ተግባር ለምን እንደተፈፀመና ሃላፊነቱን የሚወስድ አካል ማን ነው በማለት ምሬታቸውንና አቤቱታቸውን ቢያሰሙም ተገቢ ምላሽ የሚሰጥ አካል እንዳላገኙና እስከ አሁን ወደ መማር ማስተማር ስራቸውም እንዳልተመለሱ ያገኘነው መረጃ ጨምሮ ገልጿል።