Friday, March 6, 2015

በተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ/ትህዴን/ ፓምፕሌቶች መበተናቸውን ምንጮቻችን ከቦታው ገለፁ።



    በተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ትህዴን/ መልእክት የያዘው በራሪ ወረቀት በህዝቡ እጅ ደርሶ እንዲነበብ መብቃቱን የገለጸው መረጃው ፓምፕሌቱ ከተሰራጨባቸው ቦታዎች ለመጥቀስ ያህልም የካቲት 14/ 2007 ዓ/ም ላይ በአዲግራት ዩንቨርስቲና ማሃል ከተማ ውስጥ የተበተነ ሲሆን የካቲት 19/2007 ዓ/ም በመቀሌ ከተማ በቀዳማይ ወያነ፤ መስፍን ኢንጂነሪንግ፤ በራህሌ ሆቴልና ቤት ህንፀት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ መበተኑን ተገልጿል።
    የፓምፕሌቱ መልእክት የትግራይ ህዝብ ለ17 ዓመታት ያህል  ትግል ቢያካሂድም በህወሃት መሪዎች መካዱና ስልጣን ላይ ያለው ገዢው የህወሃት ኢህአዴግ ቡድን እድሜውን ለማራዘም ሲል ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ይሆናል ብሎ እየተናገረለት ያለውን ምርጫ ህዝቡ ተግባር ላይ የማይውልና ከሃቅ ውጭ እንደሆነ ተረድቶ ወሳኝና አማራጭ የሌለውን የትጥቅ ትግል እንዲከተል የሚል ፅሁፍ እንደነበረና ይህንን ፅሁፍ አንብቦ የተረዳውን ህዝብም የመልእክቱን ትክክለኛ ይዘት በመረዳት ደስታውን መግለፁንና በአንፃሩ የህወሃት ባለስልጣናትና ካድሬዎቹ ግን ከባድ ስጋት ላይ ወድቀው እንደሚገኙ ምንጮቻችን በላኩት መረጃ ለማወቅ ተችሏል።