Friday, March 6, 2015

በተለያዩ የሃገራችን ክልሎች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የምርጫ ካርድ ውሰዱ አትበሉን ካርዱ በእጃችሁ ነው ያለው እራሳችሁ እንደፈለጋችሁ ማድረግ ትችላላችሁ የሚል ምላሽ ለኢህአዴግ ባለስልጣናት እየሰጧቸው እንደሚገኙ ተገለፀ።



    የኢህአዴግ ባለስልጣናት በአሁኑ ሰዓት ለሁሉም የሃገራችን ህዝቦች የምርጫ ካርድ ያዝ እያሉ ነጋ ጠባ እረፍት ከልክለውት እንደሚገኙ የገለፀው ይህ መረጃ ሌሎች ድርጅቶች እንዳይመረጡ  እየተደረገ ያለውን አፈናና ረገጣ የተመለከተው የሃገራችን ህዝብ በበኩሉ ለማን ለመምረጥ ነው ካርድ የምንይዘው የምርጫ ካርዱ በእጃችሁ ስለሆነ እንዳመላችሁ ሳትመረጡ ተመረጠናል ብላችሁ ለምን አትናገሩም እያሏቸው እንደሚገኙ የደረሰን መረጃ አመለከተ።
    በኢህአዴግ ብልሹ አስተዳደር የተማረረው የኢትዮጵያ ህዝብ የስርዓት ለውጥ እየፈለገ ያለ ቢሆንም ስርዓቱ በሚያካሄደው አስመሳይ ምርጫ ግን ለውጥ ይመጣል የሚል እምነት ስለሌለው ዳግመኛ የድራማቸው መሳሪያ ከመሆን ለመዳን እራሳችሁ መራጭ እራሳችሁ ተመራጭ ስለሆናችሁ የምርጫ ካርዱን ለህዝብ መስጠት ለምን አስፈለገ ከናንተ የምንጠብቀው አዲስ ነገር የለም እያላቸው እንደሆነ መረጃው አክሎ አስርድቷል።