Friday, March 6, 2015

በአብይ ዓዲ ከተማ የሚገኙ የገዥው ህወሃት ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ካድሬዎች የምርጫ ካርድ ያልያዘ ሰው ማህበራዊ አገልግሎት እንዳያገኝ እያደርጉት መሆናቸውን ከስፍራው የደርሰን መረጃ አመለከተ።



በትግራይ ክልል ማዕከላዊ ዞን ዓብይ አዲ ከተማ የሚገኙ አስተዳዳሪዎች ጥር 24/2007 ዓ/ም የከተማን መሬት ለህዝቡ ለማደል ፕሮግራም እንዳላቸው ቀድመው ማሳወቃቸውን የገለፀው መረጃው ሆኖም ግን የከተማው ነዋሪ ህዝብ የምርጫ ካርድ በመውሰድ ላይ ፈቃደኛ ባለመሆኑ መሬት መታደል ከተፈለገ በመጀመሪያ የምርጫ ካርድ መያዝ ይኖርበታል በማለት የማደል ተግባሩን አቁመውት እንደሚገኙ ታውቋል።
   ከዚህ ውጭ በከተማዋ የሚገኙ ካድሬዎች የካቲት 8 /2007 ዓ/ም የከተማዋ ነዋሪ ህዝብ ከህወሃት ጎን እንዳለና ህወሃትን እንደሚመርጥ ለማስመሰል ሰላማዊ ሰልፍ አካሂዱ በማለት እያስገደዱ ሲሆን ሱቆችንና ቁርስ ቤቶች የመሳሰሉትን ድርጅቶችን እየዘጉ ሰርተን እንዳንበላ በዚህ ድርጅት ከፍተኛ እንግልት እያጋጠመን ነው በማለት ምሬቱን እየገለፀ እንደሚገኝ መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።