Wednesday, March 25, 2015

በኦሮሚያ ክልል በነቀምትና ደዴሳ ከተሞች የሚገኝ ወጣት ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ እያደረገው ያለውን ቅስቀሳ እንደተቃወሙት ታወቀ፣



በአገኘነው መረጃ መሰረት ከመጋቢት 1/ 2007 ዓ/ም ጀምሮ በነቀምትና በዴዴሳ ከተሞች ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ስራ-አጥ ወጣቶችን በመሰብሰብ መሬት ለሌለው እናድላለን የእርሻ ትራክተር በነፃ እናድላለን የመኪና ሹፌሮችንም መንግስት በራሱ ይቀጥራልችኋል ማዳበሪያ በ1300 ይሸጥ የነበረ 500 ብር ይቀነስላችኋል እና የመሳሰሉትን የገዥው መንግስት ካድሬዎች ቢቀሰቅሱም ይህ ቅንነት የለውም በማለት ወጣቶች እንደተቃወሙት ሊታወቅ ተችሏል፣
የወጣቶች የመቃወሚያ ምክንያትም እስካሁን የት ነበራችሁ ዛሬ ሁሉን ችግራችንን እንፈታላችኋለን የምትሉን አሁን ምርጫ ስለተቃረበ እስከሚያልፍ ነው እንጂ ካለፈ በኋላ አታስቡንም ቃላችሁን እንደምትክዱን እናውቃለን በማለት የተቃወማቸው መሆኑን የደረሰን መረጃ አስረድቷል፣