Friday, March 6, 2015

በአዲስ አበባ ከተማ ኣወርየ በተባለው አካባቢ ማህበራዊ ህይወታቸውን አስመልክተው ተሰባስበው እየተነጋገሩ የነበሩት ነዋሪዎች በፖሊስ አባላት ከባድ ድብደባ የደረሳቸው መሆኑን ተገለፀ።



    ከከተማው የደረሰን መረጃ እንዳስረዳው የካቲት 5/2007 ዓ/ም በአዲስ አበባ ከተማ ኣወርየ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሚገኙ ነዋሪዎች አንድ ላይ ተሰባስበው ማህበራዊ ኑሮአቸውን አስመልክተው እየተነጋገሩ በነበሩበት ሰዓት የኢህአዴግ ስርዓት ፖሊስ አባላት አካባቢውን ድንገት በመክበብ ምን ለማድረግ ተሰባሰባችሁ በማለት በመሳርያ አፈሙዝ  እያስፈራሩ ክፉኛ እንደደበደቧቸው ተገለጸ።
    ፖሊሶቹ የፈፀሙትን ድብደባ የታዘበው የአካባቢው ህዝብ ከመኖርያውና እየሰራበት ከነበረው የስራ ቦታ በመውጣት በሰላማዊው ህዝብ ላይ ግፍ መፈፀምና ከጎረቤት ሰው ጋር አትነጋገሩ የሚባልበት ዘመን መጣብን እያለ ብሶቱን እያሰማ መሆኑን መረጃው አክሎ አስረድቷል።