Tuesday, May 26, 2015

የውቅሮ ክልተ አውላሎ ከተማ ህዝብ ጥራቱን ያልጠበቀ ውሃ በመጠቀሙ ምክንያት በውሃ ወለድ በሽታዎች እየተሰቃየ እንደሚገኝ ምንጮቻችን ገለፁ።



   እንደምንጮቻችን መረጃ መሰረት በውቅሮ ክልተ አውላሎ ከተማ ጥራቱን የጠበቀ ውሃ ከጠፋ ረዥም ጊዜ ያስቆጠረ ሲሆን ይህንን ችግር አይቶ መፍትሄ የሚሰጥ አካል ባለመኖሩ የተነሳ ህዝቡ ህይወቱን ለማዳን ሲል ጥራቱን ያልጠበቀና የተበከለ ውሃ ስለሚጠቀም በተለያዩ የውሃ ወለድ በሽታዎች ተይዞ እየተሰቃየ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል።
    ነዋሪው ህዝብ ጥራቱን የጠበቀ ውሃ ማጣቱን የተገነዘበው አረና/ መድረክ በበኩሉ ከግንቦት 3 እስከ 6 2007 ዓ.ም ህብረተሰቡን ሰብስቦ በስልጣን ላይ ያለው ስርዓት ችግራችሁን የሚፈታላችሁ ካልሆነ እኛ ለጊዜው አራት ቦቲ ውሃ የሚያመላልሱ መድበን ጊዜያዊ መፍትሄ እንሰጣችሁ አለን ማለታቸውን የሰሙት የህወሃት ኢህአዴግ ካድሬዎች የአረና /መድረክን  ወክሎ ስብሰባ ሲመራ ለነበረው የስየ አብረሃ ወንድም ለሆነው ምህረትአብ አብረሃ ከስብሰባው አስፈራርተው ሲወስዱት የተመለከተው ነዋሪው ህዝብ ይህንን ሰው መንካት ማለት እኛን መንካት ማለት ነው አንድ ጉዳት ከደረሰበት አመፅ እናካሄዳለን በሚሏቸው ሰዓት ለጊዜው ለማስመሰል ሲሉ ፈርተው እንደተውት ከምንጮቻችን ያገኘነው መረጃ አመለከተ።