Thursday, May 21, 2015

የሽሬ እንዳስላሴ ከተማ ነዋሪ ህዝብ ለህወሃት ማጠናከሪያ የሚውል ገንዘብ እንዲያዋጣ በአስተዳዳሪዎች ቢገደድም ዛሬ ይሁን ነገ የምናወጣው ነገር የለም በማለት መቃወሙን ለማወቅ ተችሏል።




   በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ  ዞን ሽሬ እንደስላሴ ከተማ የሚኖረው ህዝብ የህወሃት ኢህ,አ.ዴ.ግ ካድሬዎች ግንቦት 5ቀን 2007 ዓ/ም በመሰብሰብ ለድርጅታቸው ማጠናከሪያ የሚሆን ገንዘብ እንዲያዋጡ ማስፈራራት የተሞላበት ጥያቄ መጠየቃቸውን የገለፀው መረጃው ተሰብሳቢው ህዝብ በበኩሉ ለህወሃት ገንዘብ እያዋጣን ልንኖር ነወይ? የራሳችን ኑሮ ከብዶን አጋዥ እየፈለግን ነው በማለት ተቃውሞአቸውን እንደገለፁላቸው ለማወቅ ተችሏል።
     ስብሰባውን ይመራ የነበረው የትግራይ ክልል ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን አስተዳዳሪ ጎይትኦም ይብራህ አንከፍልም በማለት የተቃወሞ ሃሳባቸውን በመድረክ ላይ የገለፁት ነዋሪዎችን አቶ አባዲ ካህሳይና ሳልህ አህመድ የተባሉ የሚገኙባቸው ወገኖች እነዚህ “ምርጫው በሰላም እንዳይጠናቀቅ የሚመኙ ፀረ ሰላም  ናቸው” በማለት ለ3 ሰዓታት ያህል በተሰብሳቢው መካከል ቆመው እንዲቀጡ ካደረገ በኋላ ተከታተሏቸው በማለት ከህዝቡ እንዲነጠሉ መልዕክት ማስተላለፉን ለማወቅ ተችሏል።