Sunday, September 20, 2015

በዚህ ሳምንት ውስጥ የህወሃት ኢ.ህ.አ.ዴ.ግን ስርዓት በመቃወም በርካታ ወጣቶች ወደ ትግራይ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ ድርጂት መቀላቀላቸውን ከማሰልጠኛ ማዕከል የደረሰን መረጃ አመለከተ።



በደረሰን መረጃ መሰረት የወያኔን ከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ በመቃወም በርካታ  ወጣቶች ወደ ማሰልጠኛ ማዕከል መቀላቀላቸውን የገለፀ ሲሆን የተወሰኑትን ለመጥቀስ ያህል
1 ተክላይ ታፈረ ገብረዋሂድ ከትግራይ ማዕከላዊ ዞን ናዴር አዴት ወረዳ አዲ ላኪያን ቀበሌ አዲ በዛ አካባቢ
2 በሪሁ ገብረየሱስ ሃድጉ ከትግራይ ምስራቃዊ ዞን ጉሎ መከዳ ቀበሌ አዲስ ተስፋ ሰፈር ደንጎሎ ከተባለው መንደር
3 ነፀረ-አብ አባዲ ፍስሃ ከሰሜናዊ ምዕራብ ዞን ታህዳይ አድያቦ ወረዳ ገመሃሎ ቀበሌ ሁመር ከተባለው ሰፈር
4 ፍስሃ ገብረስላሴ ገብረ መድህን ከማዕከላዊ ዞን አህፈሮም ወረዳ ቤተ ገበዝ ቀበሌ ዝባን እንዳቦይ ገብራት ከተባለው  አካባቢ
5 ጉዑሽ ሃይለ ገብረስላሴ ከስሜን ምዕራብ ዞን ታህታይ ቆራሮ ወረዳ ማይ አድራሻ ከተባለው ቀበሌ
6 አወት ገዛኢ ፈዳይ ከትግራይ ምስራቃዊ ዞን ጉሎመከዳ ወረዳ ዛላንበሳ ከተማ
7 ክብሮም ገብረ ፃድቅ ረዳ ከማዕከላዊ ዞን መረብ ለኸ ወረዳ አድፍታው ቀበሌ አዲ ቀረዲሂም ከተባለ መንደር
8 በሪሁ አብረሃ ተላ ከትግራይ ደቡባዊ  ዞን አምባላጀ ወረዳ ስስት ቀበሌ ከታረ ከተባለው ሰፈር
9 በረከት ገብረ ኪዳን ወልደማሪያም ከትግራይ ማኦከላዊ ዞን ናአዴር አዴት ወረዳ አዲ ለኪያን ከተባለው ቀበሌ
10 ሚኪኤሌ ካህሳይ በርኸ ከትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን ታህታይ አድያቦ ወረዳ አዲ ፀፀር ከተባለው ቀበሌ
11 ፀጋይ ሃፍታይ ከምስራቃዊ ዞን ክልተ አውላሎ ወረዳ ፅጌረዳ  ቀበሌ
12 ከድር ወህበይ አብራር ከሰሜናዊ ምዕራብ ዞን ታህታይ ቆራሮ ወረዳ አድ ብዘት ከተባለው ቀበሌ ብዘት አካባቢ እምቢሉ ከተባለው መንደር
13 ሃጎስ ገብረ ዮሃንስ ንጉሴ ከማዕከላዊ ዞን መረብ ለኸ ወረዳ አወት ቀበሌ
14 ግደይ ወልደሚካኤል ወልደማሪያም ከሰሜናዊ ምዕራብ ዞን ሽረ ወረዳ  ሰመማ ቀበሌ
15 አሸናፊ ገብረየሱስ ወልዱ ከምስራቃዊ ዞን ጉሎ መከዳ ወረዳ አዲስ አለም ቀበሌ አዲ ገናህ ከተባለው አካባቢ
16 ዘነበ አለም ገብረ ሚካኤል ከሰሜን ምዕራብ ታህታይ አድያቦ ወረዳ  ባድመ ቀበሌ
17 ገብረ ሂወት ጉዕሽ ገብረ መስቀል ከማዕከላዊ ዞን መረብ ለኸ ወረዳ ራማ ቀበሌ ሰፈር 03
18 መብርሃቶም ሃዲሽ ተክለ ከሰሜን ምዕራብ ዞን ላእላይ አድያቦ ወረዳ አድክልተ ቀበሌ ገዛ ስቃ ከተባለው መንደር
19 ክብሮም ተሾመ ክንፈ ከማዕከላዊ ዞን መረብ ለኸ ወረዳ ማይ ወዳምበራይ ቀበሌ አዲገባ እና ሌሎችም ሲሆኑ በተለይ ፍስሃ ገብረ ስላሴ ስርዓቱን እንዲቃወም ያስገደደውን ምክንያት ሲናገር  ስርዓቱ አገዛዙን ለማስረዘም ሲል ብድር በመስጠት ሞዴል ተሸላሚ ናችሁ ብሎ ሲያበቃ እንደገና ተገልብጦ በተላላኪዎቹ ተጠቅሞ አቶ ገብረእግዜር ጋዕሲ የተባለውን ንፁህ ዜጋ የቀፎ ንቡን በማላታይን ሲያጠፉ በማየቱ መሆኑን ገልፀዋል።
ሰልጣኝ ጉዕሽ ሃይሉ ገብረስላሴ በበኩሉ ባለፈው ምርጫ አረና የተባለውን ድርጂት የመረጡ ዜጎች ከመሬት እደላ እንደተከለከሉ ከገለፀ በኋላ ቀደም ሲልም በብድር የተሰጡ ወገኖችን ጊዜው ሳይደርስ መልሱ እያሉ እያሰሩ ያሰቃዩአቸው እንደነብር ገልፀዋል።