Wednesday, September 2, 2015

የኢህአዴግ ስርዓት መከላከያ ሚኒስተር ሰሞኑን በተጠባባቂነት አሰልጥኖ ወደ ትውልድ መንደራቸው የሄዱትን የሰራዊት አባላት እንደገና እንዲመለሱ ጥሪ ማድረጉን ታወቀ።





     በደረሰን መረጃ መሰረት የመከላከያ ሚኒስተር ባወጣው ማስታወቂያ መሰረት የትምህርት ደረጃቸው ከ 6 ክፍል በላይ፤ ዕድሜያቸው ከ 35 ዓመት በታች የሆኑ ሚሊሻዎችን ወደ መደበኛ ሰራዊት ትገባላችሁ፤ አገራችንን ለመውረር አሸባሪዎች እየተዘጋጁ ናቸው የሚል ሰንካላ ምክንያት ተጠቅሞ ማስታወቅያ ቢያወጣም ጥሪውን የሚቀበል ሰው እንዳላገኘ ለማወቅ ተችሏል።
    መንግስት በተደጋጋሚ የትምህርት ብቃት የላችሁም፤ እድሜአችሁ አርጅቷል፤ እያለ ያባረራቸውን ድጋሚ ለማስገባት ጥሪ ማቅረቡ ለህዝብ ያለውን ንቀት ያሳያል በማለት አንዳንድ ተቆርቋሪ ግለሰቦች መግለጻቸውንም መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።