Monday, October 12, 2015

የላይ አርማጭሆ ነዋሪዎች በገዢው የኢህአዴግ ቡዱን ተላላኪዎች በሆኑት ልዩ የፖሊስ ሃይል ግፋዊ በሆነ አካሄድ እየታሰሩ እንደሚገኙ ተገለፀ።



በምንጮቻችን መረጃ መሰረት በጎንደር ዞን ላይ አርማጭሆ ወረዳ የገጠር ቀበሌዎች የሆኑት ሙሴ ባንብ፤ ጀኒካው፤ ገንበራንና ሌሎች አካባቢዎች የሚገኙ ንፁኃን ወገኖች ስርአቱ ባሰማራቸው ልዩ የፖሊስ  ሃይልና ከመከላከያ ሰራዊት አባላት ጋር በመሆን አፍነው ወደ እስር ቤት እያጎርዋቸው እንደሚገኙ ከመረጃው ለመረዳት ተችሏል።
  በመሆኑም ለእስር ከተዳረጉት የገንበራ አካባቢ ነዋሪዎች የሆኑት አርሶ አደሮች ብቻ ለመጥቀስ ያህል፦
1.  አቶ አረጋው አበራ ( የምልሻ ኮማንደር የነበረ )
2.  አቶ አወቀ ጎሉ
3.  አቶ ተቀባ ብርሃን
4.  ወጣት ቴድሮስ ሙሉ
5.  ወንድሙ ሙሉና ወ/ሮ ደብሬ የኔአለም የተባሉት ንፁኃን አርሶ አደሮች ታፍነው ወደ ትክል ድንጋይ የልዩ ሃይሉ ወተሃደራዊ ካምፕ ተወስደው ከታሰሩት ገሚሶቹ እንደሆኑ መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።