Thursday, April 17, 2014

ኣብ ክልል ኣምሓራ ከተማ ጎንደር ልዕሊ 500 መንበሪ ኣባይቲ ንክፈርሱ ሓላፊ ቤት መዘጋጃ ምምሕዳር ሰሜን ጎንደር ትእዛዝ ከም ዘመሓላለፈ ተገሊፁ።

የዓዲ ጎሹ ከተማ ነዋሪዎች በኢ.ሀ.አ.ዴ.ግ ባለስልጣኖች ትእዛዝ መኖርያ ቤታቸውን በመፍረሱ ምክንያት በረሃ ላይ ተጥለው ብሶታቸውን እያሰሙ መሆናቸውን ተገለፀ።

የኢ.ህ.አ.ዴግ ሰራዊት የበላይ መኮንኖች መሳርያዎች ሸጠው ላገኙት ገንዘብ በመከፋፈሉ ላይ ሳይስማሙ በመቅረታችው ምክንያት ራሳቸው እስከ መገዳደል ደረጃ መድረሳቸው ከሰራዊቱ ውስጥ ሸልኮ የደረሰን መረጃ ኣስታወቀ።

በትግራይ ምእራባዊ ዞን ነዋሪና በስርአቱ ባለስልጣኖች መሀል እየተካሄደ ባለው የእርሻ መሬት ክፍፍል ምክንያት ትልቅ ችግር እንደተፈጠረ ከቦታው የደረሰን መረጃ አስታወቀ።

የላዕላይ አድያቦ ወረዳ አስተዳዳሪዎች የሃገርንና የህዝብን ገንዘብ ለግል ጥቅማቸው እያዋሉት እንደሚገኙ ምንጮቻችን ከአካባቢው ገለጹ።

Sunday, April 13, 2014

በኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ስርአት መከላከያ ሰራዊት ውስጥ በተከስተው ብጥብጥ ምክንያት ከ400 በላይ የሰራዊቱ አባላት በዓዲ ኮኸብ ታስረው እንደሚገኙ ከማእከላይ ዕዝ ሸልኮ የወጣ መረጃ አስታወቀ ።

የትግራይ ክልል ፀረ ሙስና ሃላፊ ለሆነው ለአቶ ብርሃነ አሰፋ ገንዘብ ያጠፋፉት ሰዎች ኦዲተሮች አጣርተው ክስ አቅርበውለት እያለ ለአራት አመታት ያክል ደብቆት እንደቆየ መጋቢት 24 / 2006 ዓ\ም በተካየደው በክልሉ የካብኔዎች ስብሰባ ላይ ተገለፀ።

የሸራሮ ከተማ አስተዳዳሪዎች በአካባቢው የሚገኙ ወጣቶችን በመሰብሰብ መንግስት ሊያስተባብራችሁ ስለተነሳ ተደራጁ እያሉ በተናገሩበት ሰአት ተሰብሳቢዎቹ የማይተገበር የውዥንብር ቃል ነው በማለት መልእክቱን እንዳልተቀበሉት ተገለፀ።

በትግራይ ክልል ለኮንዶምኒየም መስሪያ ተብሎ የተመደበ በጀት ብስራ አስኪያጆች እየተጠፋፋና የተሰሩ ህንፃዎችም ቢሆኑ ጥራት ስለ ሌላቸው አደጋ እያደረሱ መሆናቸው ተገለፀ።

በትግራይ ምዕራባዊ ዞን ቃፍታ ሑመራ ወረዳ የሚኖሩ ህብረተሰብ በህጋዊ መንገድ የተረከቡትን መሬት በስርአቱ ካድሬዎች እየተቀሙ ለሃብታሞች በመታደሉ ምክንያት ተቃውሞ ማስነሳቱ ተገለፀ።