Saturday, May 23, 2015

በአዲስ አበባ አቃቂ ክፍለ ከተማ የሚገኘው የአረቄ ፋብሪካ የኢህአዴግ ባለስልጣኖች መሆኑን ያወቁ ሰዎች እንዳቃጠሉት ታወቀ።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለምረቃ በተቃረቡበት ሰዓት የአብዛኛዎቹ ውጤት ዝቅተኛ መሆኑ ሲነገራቸው አመፅ ለማስነሳት እንደ ተደራጁ ተገለፀ።

በደባርቅ ወረዳ የአምባ ጊዮርጊስና የሰሜን ጎንደር ነዋሪዎች የምርጫ ካርድ አንወስድም ብለው በመቆየታቸው የስርኣቱ ካድሬዎች ካርድ ጠፋብን ብላችሁ ውሰዱ በማለት ያቀረቡት ጥያቄ ተቀባይነት እንዳላገኘ ለማወቅ ተችሏል።

በአማራ ክልል የሚገኙ የብአዴን ኢ.ህ.አ.ዴግ ካድሬዎች ህዝብ እንዲመርጣቸው ሲሉ ተቋማት እንሰራለን በማለት የመሰረት ድንጋይ እያስቀመጡ መሆናቸው ታወቀ።

የጎንደር ከተማ ከንቲባ ምርጫው በተቃረበበት ሰዓት የመንግስት ሰራተኞችና ነጋዴዎችን በመሰብሰብ በማህበር ከተደራጃችሁ ለመኖርያ ቤት መስሪያ የሚውል መሬት ትሰጣላችሁ በማለት የማይተገበር ቃል እንደገባላቸው ተገለፀ።

ኣብ ከተማ ነቀምቴ ዝርከቡ ዕጡቛት ገዛኢ ስርዓት ኢህወዴግ ኣብ ልዕሊ ተምሃሮ ዩኒቨርሲቲ ናይ’ታ ከተማ ቡምባ ተኲሶም ጉድኣት ከም ዘውረዱ ተገሊፁ።

ኣብ ክልል ትግራይ ዝርከቡ መናእሰይ ናብ ዉትህድርና ክኣትዉ ብሰበ ስልጣን ጉጅለ ህወሓት/ኢህወዴግ ዝካየድ ዘሎ ጎስጓስ ብህዝቢ ዓብዪ ተቓዉሞ ይገጥሞ ከምዘሎ ተፈሊጡ።