Pages

Wednesday, February 20, 2013

በምእራብ ጎጃም ዞን ፤ በፍኖተ ሰላም ከተማና አከባቢዋ 7 የካቲት 2005 ዓ/ም ከፌደራልና ከአማራ ክልል በተላኩ ሃላፊዎች በተካሄደው ስብሰባ የቀረበው አጀንዳ በኗሪው ህዝብ ዘንድ ተቀባይነት አለማግኘቱን ቷውቋል፣



የአማራ ክልል የህዝብ ግንኝነት ሃላፊና የፌደራል ምክር ቤት አባል የሆኑት ወ/ሮ ሙሉነሽ አንድ ላይ በመሆን በመሩት ስብሰባ የፍኖተ ሰላም ከተማና የአከባቢዋ ህዝብ ለምን የምርጫ ካርድ መውሰድ አልቻሉም በሚል የቀረበው ሃሳብ በስብሰባው ተሳታፊዎች ተቀባይነት አልማግኘቱን ከቦታው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል ፣
በደረሰን ዘገባ መሰረት ተሰብሳቢውቹ በሚደረገው ውድድር እኛን የሚወክል ድርጅት እስከሌለ ድረስ ማንን ለመምረጥ ነው ካርድ የምወስደው ፥ መርጫው በሃሰትና በማጭበርበር እየሆነ ያለው ፣ መረጥንም አልመረጥንም እናንተ እንደሆነ ስልጣን የሙጥኝ ማለታችሁ አይቀርምና ከምርጫው የምናገኘው ትርፍ የለም ሲሉ ከፈደራልና ከክልል ለተላኩት ልእካን እንደመለሱላቸው ለማወቅ ተችለዋል ፣
በተመሳሳይ በምእራብ ጎጃም ዞን ፤ የቡሬ ከተማ ህዝብ በልእካኑ ቡድን የተመራውን ምርጫን የተመለከተ ስብሰባና ቅስቀሳ እንዳልተቀበለው ቷውቋል፣