Wednesday, February 20, 2013

በአንድ ለአምስት አደረጃጀት ያልተደራጀ ሰው እርምጃ ይወሰድበታል ሲሉ በአዊ ዞን መንከሻ ጉጉሳ ወረዳ የብአዴን የህዝብ አደረጃጀት ሃላፊ 8 ለካትት 2005 ዓ/ም ባደረጉት ንግግር ገለጹ፣



በደረሰን ዘገባ መሰረት ከብአዴን የተለየ አመለካከት ያላቸውን ሰዎች መያዝ በሚል አጀንዳ  የተነጋገሩ የብአዴን አባላት በልማት ሽፋን በሚካሄደው የአንድ ለአምስት አደረጃጀት ሁሉም ህዝብ መደራጀት አለበት ቢሉም ህዝቡ ፈቃደኛ ባለመሆኑ በወረዳዋ የብአዴን የህዝብ አደረጃጀት ጉዳይ ሃላፊ በአንድ ለአምስት አደረጃጀት ያልተደራጀ ማንኛውም የወረዳዋ ኗሪ እርምጃ ይወሰድበታል ሲሉ መደመጣቸው ለማወቅ ተችሏል፣
ይህ በእንዲህ እያለ በኢህአደግ ስርዓት ውስጥ በተፈጠረው ስጋት በርካታ ወታደሮች በ 14 ኡራል ወታደራዊ ተስከርካሪዎች ተጭነው ከአንካሻ ጉጉሳ እየተገነባ ወዳለው የአባይ ግድብ መግባታቸውን ቷውቋል፣