Pages

Saturday, May 18, 2013

መንግስትን በመቃወም አድማ ካደርጉ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መካከል 100 በጸጥታ ሃይሎች ተማሪዎች ተይዘው መታሰራቸው ቷውቃል፣፣



ባሳለፍነው ሳምንት የጀመረው የዩኒቨሲቲው ተማሪዎች የተቃውሞ አድማ ለመቆጣጠር መንግስት ወደ ዩኒቨርሲቲው የፌደራል ፖሊስ አባላት በመላክ አድማውን አነሳስተዋል በሚል ጥርጣሬ ከ 100 በላይ ተማሪዎችን በመያዝ በጋሞ ጎፋ ዞን በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ እንዳሰራቸው ለማወቅ ተችሏል፣፣
ተማሪዎቹ ባካሄዱት አድማ የተለያዩ አካዲያሚያዊና አስተዳደራዊ በደሎችን ያነሱ ሲሆን በአድማው ስጋት የገባው መንግስት የዩኒቨርሲቲውን ግቢ በፖሊስ እንዲከበብ አድርጓል፣ የታሰሩትን ተማሪዎችን ለመጠየቅ ወደ ታሰሩበት እስር ቤት የሄዱ የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎችንም በፖሊስ ከአከባቢው እንዲባረሩ ተደርጓል፣፣
ተማሪዎቹ ጉንበት 5,2005 ዓ/ም ከሌሊቱ አራት ሰዓት ጀምረው ባካሄዱት አድማ ካቀረባቸው ጥያቄዎች መካከል ብሄር ከብሄር መለያየት ይቁም ፤ የተበከለ ምግብ አንመገብም ፤ የትምህርት ጥራት ይረጋገጥ ፤ አስተዳደራዊ ችግር ይፈታ ፤ መብታችን ይከበር ፤ ድምጻችን ይሰማ ፤ ለጥያቄዎቻችን ተገቢው ምላሽ ይሰጥና ከዩኒቨርሲቲ ተመርቆ በኮብል ስቶን ስራ መሰማራት ፍትሃዊ አይደለም የሚሉ ይገኙበታል፣፣
   ዩኒቨርሲቲው በወታደሮች በመከበቡና ተማሪዎቹ ከግቢው ውጭ በመውጣት ተቃውማቸውን እንዳይገልጹ ስለተከለከሉ በየዶርማቸው መስኮት በመሆን ለጥያቄዎቻችን ምላሽ እካልተሰጠን ድረስ ትምህርት አንጀምርም በማለት ተቋውማቸውን በመግለጽ ላይ መሆናቸውን የደረሰን ዘገባ ጨምሮ ያስረዳል፣፣