Saturday, May 18, 2013

በአማራ ክልል ፤ አዊ ዞን ፤ የጓጉሳ ወረዳ ኗሪዎች ተመጣጣኝ ባልሆነ ዋጋ ማዳበሪያ እንዲገዙ እየተደረገ ነው፣፣



ኗሪነታቸው በጓጉሳ ወረዳ ስር በሚገኙት አራት ቀበሌዎች የሆኑ ገበሬዎችን በመሰብሰብ ምርትን ለማሳደግ ግብአትን ማሻሻል በሚል መፈክር ማዳበሪያን በውድ ዋጋ እንዲገዙ ለማድረግ ከወረዳዋ አስተዳድር አቶ ደሴ ዋለልኝ የወረደ መመሪያ በአከባቢው ገበሬዎች ተቀባይነት እንዳላገኝና ተሰብሳቢዎቹ  ስብሰባውን ረግጠው እንደወጡ ለማወቅ ተችሏል፣፣
  በሌላ በኩል በምእራብ ጎጃም ዞን ወንበርማ ወረዳ በሽንዴ ፤ ወገዳድና ኮኪ የሚኖሩ ዜጎች ከመንግስት በሚላኩ ታጣቂዎች ወከባና እንግልት እየደረሰባቸው መሆኑን ከአከባቢው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል፣፣