በደረሰን መረጃ መሰረት በአማራ ክልል፤ ደቡብ ወሎ ዞን፤ ቦረና ወረዳ፤ በእርዳታ አታለው ማዳበሪያ እንዲወስዱ ቢያደርጉም አብዛኛው አርሶ አደር ግን እንቢተኛ መሆኑን የገለጸው መረጃው አንወስድም ብለው ከታሰሩት ግለሰቦች ውስጥም ሰይድ ሙሄ፤ ወሰን መኩሪያ፤ አወል ይመርና ጀማል ሲራጅ እንደሚገኙባቸው ለማወቅ ተችሏል።
የኢህአዴግ ካድሬዎች በመላው የአገሪቱ አካባቢዎች የሚገኘውን አርሶ አደር
ማዳበርያ በውድ ዋጋ ገዝቶ እንዲከፍል ስለሚያስገድዱት ላልተፈለገ እዳና እንግልት እየተጋለጠ መሆኑን በተለያዩ የዜና እወጃችን መግለፃችን
ይታወቃል።