Pages

Sunday, December 8, 2013

በመቀሌ ከተማ የገጠር እርሻ ልማት ፅፈት ቤት በስርአቱ አማራሮች ከባድ የሙሱና ወንጀል እየተፈፀመ ነው ሲሉ የፅፈት ቤቱ ሰራተኞች ምሬታቸው በመግለፅ ላይ እንደሚገኙ ምንጮቻችን ከከተማዋ ገልጠዋል፣




በትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ ለህዝብ አገልግሎት እንድዉል የታሰበ  የገጠር እርሻ ልማት ፅፈት ቤት ንብረት  ህጋዊ ባልሆነ ሰነድ  ከጽህፈት ቤቱ ግምጃቤት፣ እንደ ውሃና መብራት ከባድና  እና መካከለኛ ጅነሬተሮች ሌሎች የእንቁላል መፈልፈያ ትላልቅ ማሽኖች  የመሚገኑባቸው በከፍተኛ የስርአቱ ባለስልጣናት እንዲወጡ በማዘዝ ለግል ጥቅማቸው እንዳዋሉት ለማወቅ ተችለዋል፣
     በሙሱናዉ ከተሰማሩ የፅፈት ቤቱ ሃላፊ አቶ ኪሮስ ቢተው መሆኑ የገለጠው ይህ መረጃ፣ እሱ እና መሳየቹ ሆኖው ከግምጃ ቤቱ አገባቡ ባልጠበቀና አድርግ አታድርግ በሚመስል መንገድ ንብረቱ እንዲወጣ በማዘዝ ለግል ጥቅማቸው ሲያዉሉት ከቆዩ በሃላ፣ ኦዲቶሮቹ እና የንብረት ተቆጣጣሪዎች ንብረቱ የት አለ ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ አናውቅም ሲሉ በመመለሳቸው በግምጃ ቤቱ የሚሰሩ ሰራተኞች  ላልተፈለገ ዕዳ  ተዳርገው በወንጀል እንዲጠየቁ በመደረጋቸው ምሬታቸው በመግለጥ ላይ እንደሚገኙ ታወቀ፣፣
 ኦዲተረቹ በበኩላቸው ለግምጃቤቱ ሰራተኞች ያለትእዛዝ  ለምን ወጪ ታድርጋላቹ የሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ የትግራይ ክልል መሪ የሚያህሉና በትእዛዛቸው የወጣ ንብረት ይክዱናል የሚል ግምት አልነበረንም በማለት ባልፈፀሙት በላያቸው የወረደ እዳና የዉንጀላ ክስ እንዳስገረመላቸው  በተደረገው  ስብሰባ ላይ ገልጠዋል፣፣