Monday, August 25, 2014

በኦሮሚያ ክልል በወሊሶ ከተማ በህዝቡና በፖሊስ አባላት መካከል በተፈጠረ ግጭት ምክንያት በርካታ ሰላማዊ ዜጎች ለሞትና ለአካል ጉዳት እንደተጋለጡ ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመለከተ።

በትግራይ ምእራባዊ ዞን የሚገኙ አርሶ አደሮች በእርሻ መሬታቸው የዘሩትን ሰሊጥ ነሓሴ 1/ 12/ 2006 ዓ/ም የሱዳን ሰራዊት የተዘራውን ገልብጠው ማሽላ እንደዘሩት ምንጮቻችን ከአከባቢው ገለፁ።

በትግራይ ማዕከላዊ ዞን ቆላ ተምቤን ወረዳ የመላቅመ ቀበሌ ነዋሪዎች ከሚኖሩበት ቀያቸው በአካባቢው አስተዳደር እንዲፈናቀሉ እየተገደዱ መሆናቸውን ከአካባቢው የሚገኙ ምንጮቻችን አስታወቁ።

ገበያን ለማረጋጋት ተብለው በአዲስ አበባ ውስጥ መንግስት የከፈታቸው ሱቆችና መጋዝኖች የስርአቱ ባለስልጣኖች ከነሱ ጋር ለሚተባበሩ ሃብታሞች እየሸጡሏቸው መሆናቸውን የተገኘውን መረጃ አስታወቀ።

የአዲስ አበባ ነጋዴዎች የገበያ ዋጋ እንዲንር የተቃዋሚዎች ስራ እያሳለጣችሁ ናችሁ በሚል ምክንያት በአስተዳደሩ የንግድ ድርጅታቸው እየታሸገ መሆኑን ምንጮቻችን አስታወቁ።