Sunday, December 8, 2013

በባህርዳር ከተማ የከተሞች በአል ምክንያት በማድረግ የአገርንና ህዝብ ገንዘብ እነደባከነ ተገለፀ፣




ይህ ሕዳር 11/ 2006 ዓ.ም የትካሄደ የከተሞች ቀን ለባኣሉ ማድመቅያ ተብሎ በባህርዳር  ከተማ የወጣ በአስር ሚልዮን የሚገመት ገንዘብ ከአገሬቱ ኢኮኖሚ የማይመጣጠን መሆኑ የገለጡት የከተማው ነዋሪዎች፣ ይህ  የባከነው ገንዘብ የእለት ጉርሻ አጥቶ በስቃይ እየኖረ ላለው ድሓ ህዝባችን እርዳታ መዋል ይገባው ነበር ሲሉ ጨምረው አስረድተዋል፣
  የባህርዳር ከተማ ነዋሪዎች ለባኣሉ አስመልክተው የሰጡት መረጃ የአማራ ክልል ባለስልጣናት በባኣሉ ለተገኙት የህንድ ተወላጆች እና ሌሎች ዜጎች መሸለማቸው ለፖለቲካ ፍጆታ ሲባል በቤትህ ያለ የተቸገረ ህዝብ ትተህ ለባእድ ሽልማት መስጠት ተገቢ ኣይደለም ሲሉ ኣቶ ገዘሀኝ ኣይጠገብ የተባሉ የህዝብ ተወካይ፣ የስርኣቱ ኣካሄድ መቃወማቸዉን ታዉቀዋል፣
  በተመሳሳይ ዜና በባህርዳር ከተማ ቀበሌ 17 በሚገኝ አምባሳደር ሆቴል፣ መገርሳ የተባለ የወያኔ ኢህኣዴግ ወታደር ሕዳር 19/ 2006 ዓ.ም ብሆቴሉ ዉስጥ ሆኖው ይጠጡ በነበሩ ባለስልጣናት የእጅ ቦምብ ወርዉሮ እደገደላቸው የጠቆመ መረጃው፣ የመቱት ባለስልጣናት ደግሞ ሻለቃ ተስፋይነህ ሃጎስ፣ ምክትል መቶ ኣለቃ ኣላቸው ተሾመ፣ ሃምሳአለቃ ጌታቸው ሞላ የተባሉ እንደሆኑ እና ከሆቴሉ ሰራተኞችም የቆሰሉ እንዳሉ የደረሰን መረጃ ኣመለክተዋል፣