Tuesday, November 20, 2012

በፍቃድ ስም ራሳቸው ጠፍተው የሄዱና ወደ አሃዱአቸው ያልተመለሰው የኢህአዴግ ወታደሮች እየታደኑ እንዲያዙ እቅድ የወጣ መሆኑን የተለያዩ ምንጮች ገልፅዋል፣





    እነዚህ ቁጥራቸው በርከት ያሉ ማዕርግ ያላቸው ሰዎች ከሰሜን እዝ በፍቃድና ራሳቸው ወደ ቤተሰባቸው የሄዱ የወያኔ ወታደሮች ወደ አሀዱአቸው የማይመለሱበትን ምክንያት አስመልክቶ ምንጮቻችን እንዳብራሩት በፍቃድ ምክንያት ሲሄዱ የማይመለሱበትን ውታደርነት ሲቀጠሩ በቅጥሩ ስነ ስርዓት የተገባላቸው ቃል ሳይተገበር በመቅረቱ እና በአለው ስርዓት ያላቸው እምነት ደካማነት የተፈጠረ መሆኑን አስረድተዋል፣
   የወያኔ ኢህአዴግ ወታደሮች በቅጥር ስነ ስርዓት ላይ መጀመርያ ሲቀጠሩ በካድሬዎች የሚመራው ት/ቤት ቅስቀሳና ምክር ሲያደርግባቸው በትምህርት ደረጃችሁ መሰረት የሚመጥን የኮምፒተር ሳይንስ ትምህርትና ሌላም የሞያ  አቅማችሁን እንደታዳብሩ አስፈላጊ ስልጠና ሊሰጣችሁ ነው የሚል የሀሰት ቃል ተገብቶላቸው ስለ ነበርና አሁን በሰራዊቱ ያለው የማዕርግ አሰጣጥና ሌላም ሞያዊ ስልጠና በተቃራኒው ኢ-ፍትሀዊ ሆኖ ስለ አገኙት በስርዓቱ ተቆጭተው እግራቸው ወደ መራው እየጠፋ መሆናቸው ታውቋል፣