Monday, November 19, 2012

አምባገነኑ የኢህአደግ መንግስት በመከላከያ ሰራዊት ላይ ባለው አያያዝና በሚያደርሰው አላስፈላጊ ጫና ምክንያት በርካታ የስርዓቱ ወታደሮች በጭንቀት እራሳቸውን ሲያጠፉና ሲያቆስሉ ማየት ዕለታዊ ክስተት እየሆነ መምጣቱ ከቦታው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል፣






በደረሰን ዘገባ መሰረት በስርዓቱ የመከላከያ ሃይል ባሉ የተለያዩ ክ/ጦሮች ውስጥ በርካታ ወታደሮች ባደረባቸው ከቁጥጥር ውጭ የሆነ ጭንቀት ምክንያት እራሳቸውን ያጠፉ ሲሆን ሌሎች 20 የስርዓቱ ወታደሮች ደግሞ ባደረጉት እራስን የመግደል ሙከራ ቆስለው ከሞት ተርፈዋል ፣ ቁስለኞቹ በአሁኑ ግዜ ዓዲ-ኮኽብ በተባለ አከባቢ በሚገኝ ወታደራዊ ሆስፒታል ተኝተው በመታከም ላይ ይገኛሉ ፣
በተለያዩ ክ/ጦሮች ባደረጉት እራስን የመግደል ሙከራ ቆስለው ከሞት የተረፉና በህክምና የሚገኙ ወታደሮች ቁጥር።-
1-ከ 35ኛ ክ/ጦር-----6 ወታደሮች
2-ከ 33ኛ ክ/ጦር-----3 ወታደሮች
3-ከ 31ኛ ክ/ጦር-----4 ወታደሮች
4-ከ24ኛ ክ/ጦር-----5 ወታደሮች
5-ከ22ኛ ክ/ጦር-----2 ወታደሮች
በድምሩ 20 ወታደሮች ሲሆኑ በስርዓቱ ሰራዊት ውስጥ ከግዜ ወደ ግዜ እየተባባሰ የመጣውን እራስን የመግደልና የማቁሰል ተግባር እስካሁን ድረስ መፍትሄ ስላልተገኘለት አሁንም ቢሆን በከፋ መልኩ እየቀጠለ መሆኑ ለማወቅ ተችለዋል ፣