Pages

Friday, February 22, 2013

በኢትዮጵያ እግር ካስ ፌደረሽን ውስጥ በተስፋፋው ሙስና ስጋት ውስጥ የገቡ የፌደሬሽኑ ሽሞኞች ሃላፊነታቸውን በመልቀቅ ላይ መሆናቸው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል፣



በደረሰን ዘገባ መሰረት በኢትዮጵያ እግር ካስ ፌደሬሽን ምክትል ሃላፊ የነበሩ አቶ ተካ አሰፋ የተባሉ ዜጋ በፌደሬሽኑ ውስጥ ጉቦ ፤ እርስ በርስ መጠቃቀምና ሌሎች በግልጽና በስውር የሚፈጸሙ የሙስና ተግባራት በመንሰራፋታቸውና በህጋዊ መንገድ አንድም ስራም ቢሆን ማስፈጸም በማይቻልበት ሁኔታ ውስጥ ሆኖ መቀጠል ስላልፈለጉ ስራቸውንና ሃላፊነታቸውን በፈቃዳቸው መልቀቅ መምረጣቸውን ቷውቋል፣
በአሁኑ ግዜ በሃገሪቱ በሚገኙ የመንግስት መስሪያቤቶች ሁሉ በጉቦ በዝምድናና የመንግስት ስልጣንን አለአግባብ በመጠቀም የማይገባህን ሃብት ማጋበስ የተለመደ ተግባር ሆናል፣ ዜጎች መብታቸውን ተጠቅመው የሚገባቸውን ህጋዊ ጥቅም እንዳያገኙ የሚያደርግና ህዝብንና ሃገርን እያቆረቆዘ ያለው የኢህአደግ ስርዓትን በመቃወም በርካታ የሀገር ፍቅር ስሜት ያላቸው ወገኖች ስርዓቱን በመተውና ከተመደቡበት የመንግስት ስራና ሃላፊነት በመልቀቅ ወደ ስደት እያመሩ መሆኑ የሚታወቅ ነው፣