Pages

Saturday, May 18, 2013

በታሕታይ አድያቦ ወረዳ የሚገኙ የፖሊስ አባላት ከትህዴን ጋር ግንኝነት አላችሁ በሚል ሰበብ ዜጎችን በማዋከብና በማሰር ላይ እንደሚገኙ ከቦታው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል፣



በደረሰን ዘገባ መሰረት በሰ/ምዕራብ ትግራይ ፤ በታሕታይ አድያቦ ወረዳ ፤ የባድመ ከተማ የፖሊስ ሃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ሃይሉ አቶ ብርሃነ ተኽሉ የተባሉ የከተማዋ ኗሪ የሚገኙበት በርካታ ሰዎችን ከትህዴን ጋር ግንኝነት አላችሁ በሚል ሰበብ ለሦስት ቀናት አስረው ሲያስፈራሯቸው ከቆዩ ብሁዋላ እንደለቀቅዋቸው ለማወቅ ተችሏል፣
   ትህዴን እያደረገው ባለ እንቅስቃሴ በታላቅ ጭንቀትና ውጥረት ውስጥ የሚገኙ የወረዳዋ የመስተዳድር አባላት የአይናቸው ቀለም አላምር ያላቸው ሰላማዊ ሰዎችን በመያዝ ህጋዊ ባልሆነ ቦታዎች አስረው ማሰቃየት ተያይዘውታል ፣ እንዲህ ባለው ህግ አልባ አሰራር ከትህዴን ጋር ግንኝነት አላችሁ በሚል የተያዙና የታሰሩበትን ቦታ በመቀያየር ለአንድ ወር ሙሉ አስረው ከለቀቃቸው በርካታ ሰዎች መካከል ከላይ በስማቸው የተጠቀሱት ግለሰብ ልጅ ዳኒኤል ብርህነ ተኽሉ ይገኝበታል፣