Saturday, May 18, 2013

የትግራይ የጦር ጉዳተኞችን ተሰማርተውበት ከነበረው የስራ ቦታ በማስነሳት በሌሎች እንዲተካ እየተደረገ መሆኑን ቷውቃል፣



በሰ/ምዕራብ ትግራይ በሸራሮ ከተማ መናሃሪያና በሌሎች የስራ ቦታ ተሰማርተው ቤተሰባቸውን ሲያስተዳድሩ የቆዩ የጦር ጉዳተኞች በከተማዋ የመስተዳድር አካላት ከተሰማሩበት የስራ ቦታ እየተነሱ ከመስተዳድሩ ጋር ቅርበት ላላቸው ሰዎች እየተሰጠ መሆኑን ከደረሰን ዘገባ መረዳት ተችሏል፣
ከተባረሩት የጦር ጉዳተኞች መካከል።-
1-አቶ ኪሮስ ገብረህይወት
2-አቶ ክፍሎም ገብረማሪያም(ነባር ታጋይ)
3-አቶ መርዙ ንጉሰ
4-አቶ መሓመድ ስዒድ (ለረጅም ግዜ አባል የነበረ)
5-አቶ ይርጋአለም የማነ
6-አቶ መኮነን የሚባሉ የሚገኙባቸው ሲሆን እነዚህ በከተማው መናሃሪያና ሌሎች የስራ ቦታዎች ለረጅም ግዜ እየሰሩ ቤተሰቦቻቸውን ሲረዱ የቆዩ ሲሆን አሁን ግን ከነበሩበት ስራ በመባረራቸው ምክንያት እራሳቸውንና ቤተሰቦቻቸውን በችግር ላይ ወድቀው ይገኛሉ፣
ይህ በእዲህ እያለ በሸራሮ ከተማ ጥራቱ ባልጠበቀ ንጹህ የመጠጥ ውሃ በርካታ የከተማዋ ኗሪዎች ለተለያየ የውሃ ወለድ በሽታዎች ተጋልጠው ህክምና ፍለጋ ወደ ሆስፒታል የሚመላለስ ሰው ቁጥር ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ መምጣቱን ለማወቅ ተችሏል፣
የከተማዋ ኗሪ ቀደም ሲል ለከተማ የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ተመድቦ የነበረ በጀት በከተማዋ የመስተዳድር አባላት መጠፋፋቱንና ወንጀለኞቹ ተይዘው ወደ ህግ ካለመቅረባቸው በተጨማሪ የከተማዋ የውሃ ችግርም አለመፈታቱን በምሬት ይናገራሉ፣