Pages

Sunday, January 19, 2014

በኦፍላ ወረዳ ለውሃ ጉድጓድ ማስቆፈርያ ተብሎ የተመደበ 12 ሚልዮን ብር ተጠፋፍቶ ለባለ ስልጣናት ጥቅም እንደዋለ የተገኘው መረጃ ኣስታወቀ፣




በደቡብ ትግራይ ዞን ኦፍላ ወረዳ በ 2006 ዓ.ም ህዝባዊ ኣገልጋሎት  ለሚሰጥ የወሃ ጉድጓድ ማስቆፈርያ ተብሎ ከተመደበ 12 ሚልዮን ብር፣ ሁለት የውሃ ጉድጓድ ብቻ ከተቆፈረ በኋላ፣ የተመደበው ገንዘብ ተጨርሰዋል በሚል ምክንያት ስራው መቆሙ የታዘበ የኦፍላ ወረዳ ነዋሪ ህዝብ፣ ድሮም እናንተ ለኛ ለመጥቀም ብላቹ የመደባቹሁት ገንዘብ ኣልነበረም። በልማት ስም ባጀት መድባቹህ ለራሳቹ ልትጠቀሙበት ታስቦ የተደረገ ነው፣ ዜሬም ይሁን ነገ ከናነተ የገኘነውና የምናገኘው ጥቅም የለም በማለት በስርኣቱ ያላቸው ጥላቻ እየገለፁ እንደሚገኙና፣ የተቆፈረ ሁለት ጉድጓድም ቢሆን የሚረባ ወሃ የለዉም በማለት የተቆጡ ከ 500 በላይ የወረዳዋ ነዋሪዎች በጥር 1- 2006 ዓ.ም ለስርኣቱ በመቃወም ባካሄዱት ተቃዉሞ ሰልፍም፣-
       በህዝብ ስም ወጪ ተደርጎ የተጠፋፋው ገንዘብ በፍጥነት ይመለስ የተቆፈሩት ሁለት የውሃ ጉድጓድም ለህዝብ ማታልያ እንጂ ከወጣ ባጀት ሲነፃፀር 10% ( ፐርሰንት ) ኣይሆንም፤ በስልጣን ላይ ያሉ ኣመራሮች ለጥቅማቸው እንጂ ለህዝብ ጥቅም የሚቆረቆሩ ኣይደሉም፤ የህዝብ ችግር ከግዜ ወደ ግዜ እየጨመረ ሲሀድ መፍትሔ የሚሰጥ ኣካል ግን ኣልተገኘም የሚሉና ሌሎች መፈክሮች እንዳሰሙ ከተገኘው መረጃ ለማወቅ ተችለዋል፣፣
     ለተቃዉሞ ሰልፉ ኣስተባበረው ከመሩት የወረዳዋ ነዋሪዎች ኣቶ ሓድሽ ታከለ። ኣቶ ታደሰ ብያርግልኝ፤ ወይዘሮ ሓዳስ ሹምየ፤ ወይዘሮ ሰላም በርሀ። ኣቶ ያሲን ትኩእና ኣቶ መረስዕ በይኑን በጋራ በመሆን። ህዝቡ በጎደና ወጥቶ ችግሮቹ በስርኣቱ ያለው ፀረ ህዝብ ጥላቻ በተቃዉሞ ሰልፍ እንዲገልፅ የተቻላቸውን ኣስተዋፀኦ እንዳደረጉ የደረሰን መረጃ ኣስገነዘበ፣