Saturday, January 25, 2014

በየግዜው እየተቀያየረ ባለው የትምህርት ስርኣት ምክንያት ባለፈው 22 ኣመታት ባገራችን ውስጥ የሚገኙ ተማሪዎች ውጤታማ መሆን እንዳልቻሉ የተገኘው መረጃ ኣስታወቀ፣




      የኢህኣዴግ መንግስት ስልጣን ከተቆጣጠረበት ግዜ ጀምሮ ጥራት ያለውና ደረጃውን የጠበቀ የትምህርት ስርኣት ባለመከተሉ ምክንያት፤ በተለያየ የትምህርት ደረጃ የሚገኙ ተማሪዎች ኣስፈላጊ የሆነ ትምህርትና ብቃት ጨብጦው ከከፍተኛ ትምህርት ቤቶች ተመርቆው ሊወጡ ባለመቻላቸው፤ ኣስፈላጊ ላልሆኑ ክፍያዎች እንዲጋለጡ ምክንያት እንደሆነ በመቀሌ ከተማ ውስጥ የሚገኙት የፖሊቴክኒክ ተማሪዎች ገለፁ፣
      ባሁኑ ወቅት በኣገራችን ውስጥ ያሉት ተማሪዎች ለስሙ ተምረዋል ይባሉ እንጂ፤ ሃላ ቀርና ከዘመኑ የማይሄድ ትምህርት ስለ ሚሰጣቸው በተግባር የሚማሩትም ከዘመኑ ቴክኖሎጂ ጋር ትስስር ያለው ባለመሆኑ፤ ባገሪቱ እድገት ላይ የግሉን ኣስተዋፅኦ እንዳያበረክት ማነቆ ሆነዋል ያለው መረጃው፤ በሞያው የተሰማሩ ኣካላት በፊናቸውም ጥራት ያለው የትምህርት ስርኣት ሳይዘረጋና በእውቀት የታነፀ ወጣት ሳይኖር ኣገራችን ካለችበት የድህነት ኣዘቕት የሚያላቅቅ ቀልጣፋ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ እንደማይቻል በተደጋጋሚ እየገለፁ መቆየታቸው መረጃው ኣክሎ ኣስረድተዋል፣