Pages

Thursday, January 30, 2014

በትግራይ ምእራባዊ ዞን ሁመራ ከተማ ውስጥ አዲስ የሚልሻ አባላት ለመመልመል ታስቦ የተካሄደው ስብሰባ ህዝቡ እንዳልተቀበለውና ከስብሰባው ተበትኖ መሄዱ ከቦታው የደረሰን መረጃ አስታወቀ፣




ይህን ትልቅ ትኩረት ተሰጥቶበት በዞንና በወረዳ ፀጥታ ባለስልጣናት የተመራው ስብሰባ ማንኛውም በከተማው ውስጥ የሚኖር ከ18 ዓመት በላይ የሆነ ወጣት በሚልሻነት ለመሰልጠን ፍቃደኛ ከሆነ ከመንግስት የተለያዩ ጥቅማ ጥቅሞች ማግኘት እንደሚቻል ፈቃደኛ ላልሆኑት ግን ማንኛውንም የመንግስት አገልግሎት እንደማያገኙ በመግለፅ አስፈራርተው ለመመልመል አስበው ወደ ስብሰባው ቢገቡም፤ በቦታው የተገኘው ህዝብ ግን ሚልሻ ሆነን ጥቅም ከማግኘት ፆማችን ማደር ይሻለናል ብሎ ከስብሰባው ተበትኖ እንደሄደ የደረሰን መረጃ ገለጸ፣
ይህ በእንዲህ እያለ በስልጣን ላይ ያለው የህወሓት ኢህአዴግ መንግስት የስልጣን እድሜውን ለማራዘም ሲል ዜጎች በማታለል እና የማይ ጨበጥ የሕልም ተስፋ እየደሰኮረ ለሚሊሻነትና ለመደበኛ ሰራዊቱ በሰው ሃይል ለማጠናከር እያደረገ ያለው መራራጥ በወጣቱ በአጠቃላይ በህዝብ ዘንድ ተቀባይነት ባለማግኘቱ የስርዓቱ ባለስልጣናት ስጋት ላይ መሆናቸው በመላ አገሪቱ የማነጋገርያ ርእስ ሆኖ እንዳለ ለማወቅ ተችኋል፣
    ቀደም ሲልም በሁመራ ከተማና በሌሎች የትግራይ ከተሞች በስርኣቱ የቀረቡ የመከላከያ ሰራዊት ምልመላ ፕሮግራም በህዝቡ ተቀባይነት እንዳጣና ትልቅ ተቃውሞ እንደገጠመው ይታወቃል፣