Pages

Sunday, January 19, 2014

በትግራይ ክልል ውስጥ የሚገኙ ኣካል ጉዳተኞች በመንግስት ማግኘት የሚገባቸውን ነፃ የህክምና አገልግሎት ባለማግኘታቸው ምክንያት ለተለያዩ በሽታዎች ተጋልጠው እንደሚገኙ ተገለፀ፣




ለ17 አመት ያህል ከደርግ ስርዓት ጋር በተካሄደው መራራ ትግል ከህወሃት ጎን ተሰልፈው ሲታገሉ ኣካል ጉዳተኛ በሆኑ ወገኖች  ስልጣን ላይ የወጣው የህወሃት ኢህአዴግ  ቡድን በማንኛውም መንግስታዊ ጤና ጣብያዎች ነፃ የህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ የሚናገር ቢሆንም፤ በአተገባበሩ ላይ ግን በተቃራኒ ሁኖባቸው እንደሚገኝ የችግሩ ሰለባ የሆኑትን መሰረት በማድረግ የደረሰን መረጃ አስታውቀ፣
     መረጃው በማስከትል በአደዋ ከተማና በአካባቢው የሚገኙ አካለ ስንኩላን ወገኖች የህክማና አገልግሎት ወደሚያገኙበት የመንግስት የጤና ተቋማት በሚሄዱበት ግዜ፣ የህክምና ባለሙያዎች ተቀብለው በአገባብ ህክማና ከመስጠት ይልቅ፣ በመጀመርያ የጥሮታ መታወቅያ ካርድ አሳዩን አለበለዚያ ግን እኛ የምናውቀው ነገር የለንም፣ እንደማነኛውም የአካባቢው ህብረተሰብ ገንዘባችሁን ከፍላችሁ ታከሙ እያሉ ስለሚመልስዋችው መፍትሄ ለማግኘት ሲሉ ወደከፋ ውጣ ውረድ ተጋልጠው እንደሚገኙ አስረድተዋል፣
     የስርዓቱ ባለስልጣናት በትግሉ ግዜ አካላቸውን ለጎደሉ ነፃ አገልግሎት እንዳያገኙ በማሰብ ለሚያደርጉት የተንኮል ሴራ በአደዋ ከተማና በአካባቢው ለሚገኙ የአካል ጉዳተኞች ጠበቃ የሆነው አቶ ሻምበል ፍሰሃ መረሳ፣ እነዚህ ታጋዮች አካላቸውን ጎድለው ያለጥሮታ በረሃ ላይ መጣላቸው ሳያንስ የጥሮታ ወረቀት የላችሁም እየተባሉ ነፃ የህክምና አገልግሎት እንዳያገኙ መደረጉ አግባብ አይደለም በማለትና ህዝቡን በማነሳሳት ጥር 5/2006 ዓ.ም ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ለፀጥታ አካላት ባስታውቅበት ግዜ በፀጥታ ሓላፊዎችና ብጉዳተኞቹ መካከል መረዳዳት ስላልተቻለ በአካባቢው ህብረተሰብ ግርግር ተፈጥሮ እንደሚገኝ ለማውቅ ተችልዋል፣