በትግራይ ሰሜናዊ ምእራብ ዞን በታህታይ ቆራሮ ወረዳ በዚህ ኣመት ውስጥ ከ225 ኣስተማሪዎች በላይ
ስራቸውን እንዲያቆሙ የተገደዱት ስርኣቱ ይከተለው ባለው የተዛባ ኣሰራር ተማርረው እንደሆነ የገለፀው መረጃው፣በሁኔታው ስጋት ላይ
የወደቁ የዞኑ ሃላፊዎች ምክንያቱን ለማወቅ በሚል በጥር 5/2006 ኣ/ም ባካሄዱት ስብሰባ፣ ሚዛኑን የሳተ ኣድልዎና ኣሰራር በመንሰራፋቱ፤
በቂ ደሞዝ ያለምኖሩ፤ የሚሰጣቸው ደሞዝም ቢሆን፣ ለኣባይ ግድብ፤ ለመለስ ፋውንደሽን፤ ለትግራይ ልማት ማህበርና ለህወሃት እየተባለ
ስለ ሚቆራረጥ፣ ማህበራዊ ንሮኣቸውን ለመምራት ተቸግረው እየወሰዱት ያለ እርምጃ መሆኑ ያገኘነው መረጃ እስታወቀ፣
መምህራኖቹ በማስከተል በላያቸው ላይ
እየደረሰ ያለው ብልሹ የስርኣቱ ኣስተዳደር፤ የደሞዝ ማነስ፤ ከልክ በላይ የሆነ መዋጮ፤ የንሮ ውድነትና ሌሎች ምክንያቶች ተጨምሮውበት
ተቸግረው እንዳሉ ከገለፁ በኋላ፣በዚህም ሁኔታ ችግሩን መሸከም ተስኖዋቸው የሚወዱት ያስተማሪነት ሞያ እየተው ወደ ሱዳንና ሌሎች
ኣገሮች እየተሰደዱ ያሉ ወገኖች በጣም ብዙ መሆናቸው በስብሰባው ላይ ተገልፀዋል፣
መረጃው በመጨረሻ በዚሁ ቅጥ ያጣ የስርኣቱ
ኣሰራር ተማረው ከኣንድ ቀበሌ ብቻ የማስተማር ስራቸውን ትተው የሄዱ ወገኖች ለመጥቀስ። መምህር ኣለባቸው ኣባይ የትምህርት ቤት
ዳሪክተር፤ መምህርት ትርሃስ ኣባይ፤ መምህር ፍስሃ ተክለማርያም መምህር ታዴዎስ ኣያልነህ የሚገኙባቸው ከ226 ኣስተማሪዎች በላይ
ከወረዳው ውስጥ ስራቸውን እንዳቋረጡ መረጃው ኣክሎ እስረድተዋል፣