Pages

Thursday, January 30, 2014

በፀለምቲ ወረዳ የማይ ዓይኒ ነዋሪዎች በወረዳዋ አስተዳዳሪዎች ቤታቸው እየፈረሰ እንደሚገኝ ከህዝቡ የደረሰን መረጃ አመለከተ፣




በመረጃው መሰረት በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን ልዩ ስሙ ማይ ዓይኒ በተባለ አካባቢ የሚኖሩ ዜጎች ለረጅም ዓመታት ሲኖሩበት የቆዩ ቤታችውን በወረዳዋ አስተዳዳሪዎች እየፈረሰ መሆኑን በመግለፅ፤ የዚህ ችግር ሰለባ የሆኑ ወገኖቻችን በረሃ ላይ ወድቀው ለፀሓይና ለብርድ ተጋልጠው እንደሚገኙ መረጃው አክሎ አስረድትዋል፣
     እነዚህ በህጋዊ መንገድ መሬት ተረክበው ብዙ ጉልበትና ገንዘብ አፍስሰው በመስራት ለበርካታ ዓመታት ሲኖሩበት የቆዩ ቤታችውን ያለ-ምንም ካሳና ቅድመ ዝግጅት በድንገት እንዲፈርስ ስለ ተደረገ፤ በጣም ብዙ ህፃናትና አረጋውያን  የሚገኙባቸው ዜጎቻችን በችግር ላይ ወድቀው እንደሚገኙ የተገኘው መረጃ ገልፅዋል፣
    በመጨረሻ ነዋሪዎቹ በስርዓቱ ለወረደባቸው ሃላፊነት የጎደለው ተግባር መፍትሄ ለማግኘት በመርጥዋቸው 15 ወኪሎቻቸው አድርገው ወደ ሚመለከታቸው አካላት ላቀረቡት አቤቱታ ሰሚ ማግኘት እንዳልቻሉ ከቦታው በደረሰን መረጃ ለማወቅ ተችልዋል፣