Monday, June 30, 2014

በትግራይ ምዕራባዊ ዞን በወልቃይት ወረዳ እየተሰራ ላለው የስኳር ፍብሪካ መስርያ ተብሎ በመጓጓዝ ላይ የነበረ ስሚንቶ ቦታው ላይ ሳይደርስ እየተጠፋፋ መሆኑ ታወቀ።



በወልቃይ ወረዳ እየተሰራ ላለው የስኳር ፋብሪካ መገንብያ ተብሎ በኮድ3 ኢትዮ-ትግራይ የሰሌዳ ቁጥር 15326 በሆነው የጭነት መኪና ተጭኖ እየተጓዘ የነበረው ስሚንቶ ለታሰበለት አላማ ሳይውል በሽሬ ከተማ ተራግፎ ለግል ነጋዴዎች እንደተሸጠ ከአካባቢው የደረሰን መረጃ አመለከተ።
    መረጃው ጨምሮ የመኪናዋ ሹፌር ሓጎስ አሕፈሮም የተባለ ሲሆን ይህ ሹፌር ከአቶ ጌታቸው ተላ ከተባለ የብረታብረት ድርጅት ባለቤት ከሆነው ነጋዴ ጋር በመሻረክ እንደሸጠለትና በመጋዘኑ እንዲራገፍ እንዳደረገና ለዚህ ሓላፊነት የሌለው እኩይ ተግባር የተመለከቱ የሽሬ ከተማ ነዋሪዎች ደግም እንደኮነኑት  ከተገኘው መረጃው ለማወቅ ተችሏል።
     በተመሳሳይ ለእንደዚህ አይነት ፕሮጀክት መገንቢያ እየተባለ በሃገርና በህዝብ ሃብት የሚገዛ ንብረት የፕሮጀክቱ ከፍተኛ ሃላፊዎች  ከመኪና ሹፌሮች ጋር በመሻረክ እንዲሸጥ እያደረጉ  ሃብት እንደሚሰበስቡና ይህ አስነዋሪ ተግባር ደግሞ የስርዓቱ ልዩ መገለጫ ባህሪው ስለሆነ በመላው የሃገራችን አካባቢዎች እየተሰሩ ካሉ ተመሳሳይ ፕሮጀክቶች የስርዓቱ ከፍተኛ አመራሮችና ተላላኪዎቹ የሃገርንና የህዝብን ሃብት ለግል ጥቅማቸው እንደሚያውሉት የተለያዩ የህብረተሰብ አባላት እየገለፁ መቆየታቸው ይታወል።